ኤርምያስ 20:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእግዚአብሔር ዘምሩ! ጌታን አመስግኑ! እርሱ ችግረኞችን ከክፉ ሰዎች ኀይል ይታደጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቅርቡ፤ የድኻውን ነፍስ፣ ከክፉዎች እጅ ታድጓልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታ ዘምሩ ጌታንም አመስግኑ፤ የችግርተኛውን ነፍስ ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ አመስግኑትም፤ የችግረኛውን ነፍስ ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔር ዘምሩ እግዚአብሔርንም አመስግኑ፥ የችግረኛውን ነፍስ ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና። |
ለድኾች፥ ለመጻተኞችና ለችግረኞች በችግራቸው ጊዜ መጠጊያ ሆነህላቸዋል፤ ከዐውሎ ነፋስ የሚድኑበት ተገንና ከፀሐይ ቃጠሎ የሚጠለሉበት ጥላ ሆነህላቸዋል፤ የጨካኞች ምት የክረምት ወጀብ ግድግዳን እንደሚገፋ ያለ ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከሕዝቦች ሁሉ ስለምትበልጥ ስለ እስራኤል በደስታ ዘምሩ፤ ‘እግዚአብሔር ሕዝቡን አድኖአል፤ በእስራኤል ምድር የቀሩትን ሁሉ ተቤዥቶአል’ እያላችሁ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ።”