ኤርምያስ 2:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስራኤል የተገዛች ባሪያ አይደለችም፤ የቤት ውልድም ባሪያ አይደለችም፤ ታዲያ፥ ጠላቶችዋ (በምርኮ እንደ አውሬ የሚያድኑአት) ለምንድን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤል ባሪያ ነውን? ወይስ የቤት ውልድ ባሪያ? ታዲያ፣ ስለ ምን ለብዝበዛ ተዳረገ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በውኑ እስራኤል ባርያ ነውን? ወይስ በቤት የተወለደ አገልጋይ ነውን? ስለምን ለብዝበዛ ሆነ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በውኑ እስራኤል ባሪያ ነውን? ወይስ የቤት ውላጅ ነውን? ስለ ምን ምርኮ ሆነ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ እስራኤል ባሪያ ነውን? ወይስ የቤት ውላጅ ነውን? ስለምን ብዝበዛ ሆነ? |
ወንዶችና ሴቶች ባርያዎችን ገዛሁ፤ ሌሎች የቤት ውልድ አገልጋዮችም ነበሩኝ፤ ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይበልጥ ብዙ የከብት፥ የፍየልና የበግ መንጋ አረባሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወንድ ሚስቱን ፈቶ እንደሚያባርር እኔ እናንተን ሕዝቤን ያባረርኩ ይመስላችኋልን? ይህስ ከሆነ የፍችው ደብዳቤ የት አለ? ሰው ልጆቹን ለባርነት እንደሚሸጥ እኔም እናንተን ለምርኮ አሳልፌ የሸጥኳችሁ ይመስላችኋልን? ከሆነስ ለማንኛውም አበዳሪዬ ሸጥኳችሁ? እናንተ ለምርኮ የተሰጣችሁት በኃጢአታችሁ ምክንያት ነው፤ የተሰደዳችሁትም በፈጸማችሁት በደል ነው።
ቊጣዬ እንደ እሳት እንዲቀጣጠል ስላደረጋችሁ እርሱም ለዘለዓለም ስለሚነድ የሰጠኋችሁን ርስት ሁሉ እንድታጡና በማታውቁት አገር ጠላቶቻችሁን እንድታገለግሉ አደርጋለሁ።”
ኤርምያስ ሆይ! ሕዝቡ ‘እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ነገር ያደረሰብን ስለምድን ነው?’ ብለው በጠየቁህ ጊዜ ከእኔ ተለይተው በገዛ ምድራቸው ላይ ባዕዳን አማልክትን እንዳመለኩ ሁሉ፥ እነርሱም ራሳቸው የእነርሱ ባልሆነ አገር የባዕድ ሕዝብ አገልጋዮች መሆናቸው እንደማይቀር ንገራቸው።”