ኤርምያስ 18:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። |
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ሸክላ ሠሪው ሸክላውን በፈለገው ዐይነት እንደሚሠራው፥ እኔስ በእናንተ ላይ የፈለግኹትን ማድረግ አልችልምን? የሸክላው ጭቃ በሸክላ ሠሪው እጅ እንደሚገኝ እናንተም፥ በእኔ እጅ ናችሁ።