ኤርምያስ 16:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ ሕዝቦች በሙሉ ኀይሌንና ታላቅነቴን በማያዳግም ሁኔታ እንዲያውቁት አደርጋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር መሆኔንም ያረጋግጣሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ አስተምራቸዋለሁ፤ ኀይሌንና ታላቅነቴን፣ አሁን አስተምራቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜ እግዚአብሔር፣ እንደ ሆነ ያውቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስለዚህ፥ እነሆ፥ አስታውቃቸዋለሁ፥ በዚህች ጊዜ እጄንና ኃይሌን አስታውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜ ጌታ እንደሆነ ያውቃሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስለዚህ እነሆ በዚህ ወራት አስታውቃቸዋለሁ፤ እጄንና ኀይሌንም አሳያቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ያውቃሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ፥ እነሆ፥ አስታውቃቸዋለሁ፥ በዚህች ጊዜ እጄንና ኃይሌን አስታውቃቸዋለሁ፥ እነርሱም ስሜ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ያውቃሉ። |
እኔም ልቡን ስለማደነድነው ያሳድዳችኋል፤ ስለዚህም በንጉሡና በሠራዊቱ ላይ የምጐናጸፈው ድል ለእኔ ክብር ይሆናል፤ በዚያን ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።” እስራኤላውያንም እንደ ተነገራቸው አደረጉ።
ሁሉን የምችል አምላክ (ኤልሻዳይ) መሆኔን በማስረዳት ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ተገልጬላቸዋለሁ፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) በተሰኘው ቅዱስ ስሜ አማካይነት ግን አልተገለጥኩላቸውም።
በዚህም ዐይነት ሕዝቅኤል ለእናንተ ምልክት ይሆናል፤ እርሱ እንዳደረገውም ታደርጋላችሁ፤’ ይህ በሚፈጸምበት ጊዜ እኔ ልዑል እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”
በዚያኑ ቀን ከዚህ በፊት አጥተኸው የነበረውን የመናገር ችሎታ መልሰህ ታገኛለህ፤ ከእርሱም ጋር ትነጋገራለህ ለሕዝቡም ምልክት ትሆናለህ፤ እነርሱም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”
ኤዶምን የምበቀላት በሕዝቤ በእስራኤል አማካይነት ነው፤ እስራኤላውያን በኤዶም ላይ እንደ ቊጣዬ ኀይለኛነት ይበቀላሉ፤ ኤዶማውያንም እኔ እንደ ተበቀልኳቸው ይረዳሉ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ነኝ።”
“ፕሊያዲስ” የተባሉትን ሰባቱን ከዋክብትና “ኦርዮን” ተብለው የሚጠሩትን የከዋክብት ክምችትን የፈጠረ፥ ሌሊቱን ወደ ቀን፥ ቀኑንም ወደ ሌሊት የሚለውጥ፥ የባሕሩን ውሃ አዞ፥ በምድር ላይ እንዲፈስ የሚያደርግ፥ ኀያላንንና ምሽጎቻቸውን የሚደመስስ እርሱ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።