ጒድጓድ ውሃን እንደሚያፈልቅ፥ ኢየሩሳሌምም የክፋት ሁሉ መፍለቂያ ናት፤ በእርስዋ የሚሰማው የግፍና የጥፋት ጩኸት ብቻ ነው፤ ዘወትር የሚታይባትም ሕመምና ቊስል ነው።
ያዕቆብ 3:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአንድ ምንጭ ለመጠጥ የሚሆን ጣፋጭ ውሃና መራራ ውሃ ሊፈልቅ ይችላልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአንድ ምንጭ ጣፋጭ ውሃና መራራ ውሃ ይመነጫልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአንድ ምንጭ ጣፋጭ ውሃና መራራ ውሃ ይመነጫልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምንጭስ ከአንድ አፍ የሚጣፍጥንና የሚመርን ውሃ ያመነጫልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምንጭስ ከአንድ አፍ የሚጣፍጥንና የሚመርን ውኃ ያመነጫልን? |
ጒድጓድ ውሃን እንደሚያፈልቅ፥ ኢየሩሳሌምም የክፋት ሁሉ መፍለቂያ ናት፤ በእርስዋ የሚሰማው የግፍና የጥፋት ጩኸት ብቻ ነው፤ ዘወትር የሚታይባትም ሕመምና ቊስል ነው።
ወንድሞቼ ሆይ፥ የበለስ ዛፍ የወይራን ፍሬ ሊያፈራ ይችላልን? ወይስ የወይን ተክል የበለስ ፍሬ ሊያፈራ ይችላልን? እንዲሁም ከመራራ ውሃ ጣፋጭ ውሃ ሊገኝ ይችላልን?