ያዕቆብ 2:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰውን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ” ተብሎ በቅዱስ መጽሐፍ የተጻፈውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመጽሐፍ፣ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ” ተብሎ የተጻፈውን ክቡር ሕግ ብትፈጽሙ፣ መልካም እያደረጋችሁ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጽሐፍ፥ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” ተብሎ የተጻፈውን ንጉሣዊ ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን መጽሐፍ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤” እንደሚል የንጉሥን ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን መጽሐፍ፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ እንደሚል የንጉሥን ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ፤ |
ከዚህም በኋላ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፥ “መልካም አላደረግንም! እነሆ፥ ዛሬ ታላቅ የምሥራች አግኝተናል፤ ይህንንም መልካም ዜና ደብቀን ልናስቀር አይገባንም! ይህን የምሥራች ሳንነግር እስኪነጋ ብንቈይ በእርግጥ ቅጣት ይደርስብናል፤ ስለዚህም አሁኑኑ ሄደን ለንጉሡ የጦር መኰንኖች እንንገር!”
ለእስራኤላዊ ወገናችሁ በምታደርጉት ዐይነት መልካም ነገር አድርጉላቸው፤ እንደ ራሳችሁም አድርጋችሁ ውደዱአቸው፤ እናንተም ከዚህ በፊት በግብጽ ምድር ባዕዳን እንደ ነበራችሁ አስታውሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
እግዚአብሔርም “ስለዚህች ቅል ልትበሳጭ ይገባሃልን?” አለው። ዮናስም “በእርግጥ መበሳጨት ይገባኛል፤ እንዲያውም በንዴት እስከምሞት ድረስ መበሳጨት አለብኝ!” አለ።
ጌታውም ‘መልካም አደረግህ፤ አንተ ታማኝና ደግ አገልጋይ! በጥቂት ነገር ታማኝ ሆነህ ስለ ተገኘህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ና የጌታህን ደስታ ለመካፈል ግባ!’ አለው።
ጌታውም ‘መልካም ነው! አንተ ታማኝና መልካም አገልጋይ በጥቂት ነገር ታማኝ ሆነህ ስለ ተገኘህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ና የጌታህን ደስታ ለመካፈል ግባ!’ አለው።
እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ፥ እናንተም ለእነርሱ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የሕግና የነቢያት ትምህርትም የሚሉት ይህንኑ ነው።
ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹም ሕግ መርምሮ በእርሱ የሚጸና፥ እርሱንም ሰምቶ መርሳት ሳይሆን፥ በሥራ ላይ የሚያውለው ሰው በሥራው የተባረከ ይሆናል።
ወንድሞች ሆይ፥ እርስ በርሳችሁ አትተማሙ፤ ሰውን የሚያማ ወይም በሰው ላይ የሚፈርድ ሕግን ያማል፤ በሕግም ላይ ይፈርዳል፤ በሕግ ላይ ብትፈርድ ደግሞ ፈራጅ መሆንህ ነው እንጂ ሕግን ፈጻሚ አይደለህም።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።