ያዕቆብ 2:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ ባቀረበው ጊዜ የጸደቀው በሥራ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባታችን አብርሃም ልጁን ይሥሐቅን በመሠዊያው ላይ ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ላይ ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን? |
ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃምና ወደ ወለደቻችሁ ወደ ሣራ ተመልከቱ፤ አብርሃምን በጠራሁት ጊዜ ልጅ አልነበረውም፤ ነገር ግን እኔ ባረክሁት፤ ዘሩንም አበዛሁለት።
‘እኛ የአብርሃም ልጆች ነን’ በማለት የምታመልጡ አይምሰላችሁ፤ እግዚአብሔር ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆችን ሊያስነሣለት ይችላል እላችኋለሁ።
ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ ‘አባት አብርሃም ሆይ! እባክህ ራራልኝ! በዚህ በእሳት ነበልባል ውስጥ በብርቱ እሠቃያለሁና የጣቱን ጫፍ በውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያቀዘቅዝልኝ አልዓዛርን ላክልኝ!’
እነርሱም “አባታችን አብርሃም ነው” ሲሉ መለሱለት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የአብርሃም ልጆችስ ብትሆኑ ኖሮ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር፤
እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ወንድሞቼና አባቶቼ ሆይ! እስቲ ስሙኝ! አባታችን አብርሃም በካራን ለመኖር ከመሄዱ በፊት ገና በመስጴጦምያ ሳለ የክብር አምላክ ተገለጠለትና
እንዲሁም አብርሃም ለተገረዙትም አባት ነው፤ ለተገረዙት አባት የሆነበትም ምክንያት በመገረዛቸው ብቻ ሳይሆን እርሱ ከመገረዙ በፊት የነበረውን እምነት በመከተላቸውም ጭምር ነው።
ስለዚህ ተስፋው የተመሠረተው በእምነት ላይ ነበር፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም ዘሮች ሁሉ ከእግዚአብሔር በጸጋ የተሰጠ መሆኑ በዚህ ተረጋግጦአል። ይህም ሕግን ለሚከተሉት ሰዎች ብቻ ሳይሆን እንደ አብርሃም ላመኑ ሁሉ ነው፤ በዚህም መሠረት አብርሃም የሁላችንም አባት ነውና።
አብርሃም በተፈተነበት ጊዜ ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው በእምነት ነው፤ ያ የተስፋ ቃል የተቀበለው አብርሃም አንድ ልጁን ሊሠዋው ነበር፤
ነገር ግን “አንተ እምነት አለህ፤ እኔም መልካም ሥራ አለኝ” የሚል ቢኖር፥ “እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም በሥራዬ እምነቴን አሳይሃለሁ” እለዋለሁ።
ከዚህም በኋላ የቀድሞ አባታችሁን አብርሃምን ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ከሚገኘው ምድር ጠርቼ፥ በከነዓን ምድር ሁሉ መራሁት፤ ዘሩንም አበዛሁለት፤ ይስሐቅንም ሰጠሁት፤