ያዕቆብ 2:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለምሳሌ ሁለት ሰዎች ወደምትሰበሰቡበት ቦታ ይመጣሉ፤ አንደኛው በጣቱ የወርቅ ቀለበት ያደረገና የሚያምር ጌጠኛ ልብስ የለበሰ ሀብታም ነው፤ ሌላው ያደፈ አሮጌ ልብስ የለበሰ ድኻ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወርቅ ቀለበት ያደረገና ያማረ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤአችሁ ቢመጣ እንዲሁም ያደፈ ልብስ የለበሰ ድኻ ሰው ቢገባ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወርቅ ቀለበት ያደረገና ያማረ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤያችሁ ቢመጣ እንዲሁም ያደፈ ልብስ የለበሰ ድኻ ሰው ቢገባ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወርቅ ቀለበት ያደረገና የጌጥ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤአችሁ ቢገባ፥ እድፍ ልብስም የለበሰ ድኻ ሰው ደግሞ ቢገባ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወርቅ ቀለበት ያደረገና የጌጥ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤአችሁ ቢገባ፥ እድፍ ልብስም የለበሰ ድሀ ሰው ደግሞ ቢገባ፥ |
ንጉሡም የራሱ ማኅተም ያለበትን፥ ከሃማን ጣት ወልቆ እንዲመለስ የተደረገውን ቀለበት ለመርዶክዮስ ሰጠው፤ አስቴርም መርዶክዮስን በሃማን ሀብትና ንብረት ላይ ኀላፊ አድርጋ ሾመችው።
እኛ ሁላችን በኃጢአት ረክሰናል፤ ጽድቃችንም እንደ አደፍ ጨርቅ ሆኖአል፤ ከኃጢአታችን ብዛት የተነሣ ደርቀው በነፋስ እንደሚረግፉ ቅጠሎች ሆነናል።
አባቱ ግን አገልጋዮቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ ‘ቶሎ ብላችሁ ከሁሉ የበለጠውን ልብስ አምጡና አልብሱት! በጣቱ ቀለበት፥ በእግሩም ጫማ አድርጉለት!
የሚያምር ጌጠኛ ልብስ የለበሰውን ሰው በማክበር “በዚህ በመልካሙ ቦታ ተቀመጥ” ትሉታላችሁ። ድኻውን ግን “አንተስ እዚያ ቁም፤ ወይም በእግሬ ሥር ተቀመጥ” ትሉታላችሁ፤