“ባለማወቅ ኃጢአት የሠራው መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ቢሆንና፥ ጉዳዩም ከማኅበረሰቡ ቢሰወር፥ ይህም ኃጢአት እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸው ትእዛዞች አንዱን በማፍረስ በደለኞች ቢያደርጋቸው፥
ያዕቆብ 2:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አታመንዝር” ያለው ጌታ እንዲሁም “አትግደል” ብሎአል፤ ስለዚህ ባታመነዝርም እንኳ ከገደልክ ሕግን አፍርሰሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አታመንዝር” ያለ እርሱ ራሱ “አትግደልም” ብሏልና። ባታመነዝር፣ ነገር ግን ብትገድል፣ ሕግ ተላላፊ ሆነሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አታመንዝር” ያለ እርሱ ራሱ “አትግደል” ብሏል። ባታመነዝር፥ ነገር ግን ብትገድል፥ ሕግ ተላላፊ ሆነሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባታመነዝርም፥ ነገር ግን ብትገድል፥ ሕግን ተላላፊ ሆነሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባታመነዝርም፥ ነገር ግን ብትገድል፥ ሕግን ተላላፊ ሆነሃል። |
“ባለማወቅ ኃጢአት የሠራው መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ቢሆንና፥ ጉዳዩም ከማኅበረሰቡ ቢሰወር፥ ይህም ኃጢአት እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸው ትእዛዞች አንዱን በማፍረስ በደለኞች ቢያደርጋቸው፥
“ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ይህ ነው፦ ማንም ሰው ተሳስቶ ኃጢአት ቢሠራ ወይም ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዞች አንዱን ቢተላለፍ ከዚህ የሚከተለውን ሥርዓት ይጠብቅ፦
ትእዛዞችን ታውቃለህ፤ እነርሱም ‘አትግደል፤ አታመንዝር፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፤ አታታል፤ አባትህንና እናትህን አክብር፤’ የተባሉት ናቸው።”
“አታመንዝር፤ አትግደል፤ አትስረቅ፤ የሌላ ሰው የሆነውን ማናቸውንም ነገር አትመኝ” የሚሉት ትእዛዞችና ሌሎችም ትእዛዞች ሁሉ “ሰውን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ” በሚለው በአንዱ ትእዛዝ ተጠቃለው ይገኛሉ።