የእግዚአብሔርም ኀይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን በወገቡ ዙሪያ ጠበቅ አድርጎ በመታጠቅ እስከ ኢይዝራኤል መግቢያ በር ድረስ በአክዓብ ፊት ቀድሞ ይሮጥ ነበር።
ኢሳይያስ 8:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ በሄደበት መንገድ እንዳልሄድ እግዚአብሔር በብርቱ ኀይሉ እንዲህ ብሎ አስጠነቀቀኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ብርቱ እጁን በላዬ አድርጎ የእነዚህን ሰዎች መንገድ እንዳልከተል አስጠነቀቀኝ፤ እንዲህም አለኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ብርቱ እጁን በላዬ አድርጎ የእነዚህን ሰዎች መንገድ እንዳልከተል አስጠነቀቀኝ፤ እንዲህም አለኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽኑ እጅ እንዲህ ተናገረኝ፤ በዚህም ሕዝብ መንገድ እንዳልሄድ አስጠነቀቀኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በጽኑ እጅ እንዲህ ተናገረኝ፥ በዚህም ሕዝብ መንገድ እንዳልሄድ አስጠነቀቀኝ፥ እንዲህም አለኝ፦ |
የእግዚአብሔርም ኀይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን በወገቡ ዙሪያ ጠበቅ አድርጎ በመታጠቅ እስከ ኢይዝራኤል መግቢያ በር ድረስ በአክዓብ ፊት ቀድሞ ይሮጥ ነበር።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዐመፀኞች ለሆኑ ልጆች ወዮላቸው! እኔ ባላወጣሁላቸው ዕቅድ መመራት ይፈልጋሉ፤ ከእኔም ፈቃድ ውጪ የቃል ኪዳን ውል በመፈጸም በኃጢአት ላይ ኃጢአት ይጨምራሉ።
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “ወደ እኔ በንስሓ ብትመለስ፥ እቀበልሃለሁ፤ እንደገናም አገልጋይ ትሆነኛለህ፤ ከንቱ ቃል መናገርህን ትተህ ቁም ነገር ያለውን መልእክት ብታስተላልፍ፥ እንደገና የእኔ ነቢይ ትሆናለህ፤ ሕዝቡ ወደ አንተ ይመጣሉ እንጂ አንተ ወደ እነርሱ አትሄድም።
እግዚአብሔር ሆይ! አታለልከኝ፤ እኔም ተታለልኩ፤ አንተ ከእኔ ትበረታለህ፤ ኀይልህም በእኔ ላይ እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ ሰው ሁሉ በየዕለቱ በማሽሟጠጥ ይዘባበትብኛል።
ነገር ግን “ከእንግዲህ እግዚአብሔርን አላስታውስም፤ በስሙም አልናገርም” በምልበት ጊዜ፥ ከእርሱ የተሰጠኝ የትንቢት ቃል በውስጤ እንደ እሳት ይነዳል፤ በውስጤ ሰውሬ ልይዘው ብሞክርም፤ አፍኜ ላስቀረው አይቻለኝም።