ገለባ በእሳት ብልጭታ እንደሚጋይ “ኀይለኞች ነን” የሚሉ ሰዎች ይጠፋሉ፤ እንደ ቃጠሎ እሳት በእነርሱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት የሚያቆም የለም።
ኢሳይያስ 66:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእርያ ሥጋና አይጥ፥ እንዲሁም ሌሎች አጸያፊ ነገሮች ከሚበሉት ሰዎች መካከል አንዱን ተከትለው ወደ አትክልቶቹ ቦታዎች ለመሄድ ራሳቸውን የሚለዩና የሚያነጹ በአንድነት ይጠፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወደ አትክልት ቦታዎች ለመሄድና ከተክሎቹ አንዱን ለማምለክ ራሳቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፣ የዕሪያዎችንና የዐይጦችን ሥጋ፣ የረከሱ ነገሮችንም የሚበሉ ሁሉ የመጨረሻ ፍርዳቸውን በአንድነት ይቀበላሉ” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመሀከላቸው ያለውን አንዱን ተከትለው ወደ መናፈሻ ስፍራው ለመግባት ሰውነታቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፥ የእሪያንም ሥጋ፥ አስጸያፊ ነገርንም፥ አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ፥ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በአትክልት ቦታ ውስጥ ሰውነታቸውን የሚያጠሩና የሚያነጹ፥ በምግብ ቦታም የእሪያን ሥጋ፥ አስጸያፊ ነገርንም አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመካከላቸው ያለውን እንዱን ተከትለው ወደ ገነቱ ይገቡ ዘንድ ሰውነታቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፥ የእሪያንም ሥጋ አስጸያፊ ነገርንም አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
ገለባ በእሳት ብልጭታ እንደሚጋይ “ኀይለኞች ነን” የሚሉ ሰዎች ይጠፋሉ፤ እንደ ቃጠሎ እሳት በእነርሱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት የሚያቆም የለም።
እነሆ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፤ የእግዚአብሔር ቊጣና መዓት የሚፈጸምበት ያ ቀን እጅግ አስፈሪ ነው፤ በዚያን ጊዜ በእርስዋ የሚኖረው ኃጢአተኛ ሕዝብ ስለሚደመሰስ ምድሪቱ ባድማ ትሆናለች።
እኔም እንዲህ ስል መለስኩ፦ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ይህስ ከቶ አይሁን! እኔ ከቶ ረክሼ አላውቅም፤ ከሕፃንነቴ ጀምሮ የበከተ ወይም አውሬ የገደለው ከብትን ሥጋ የበላሁበት ጊዜ የለም፤ ጸያፍ ምግብም አልበላሁም።”