ኢሳይያስ 6:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከነዚያም መላእክት አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፤ ከመሠዊያው የወሰደው የእሳት ፍም የያዘበት ጒጠት በእጁ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከሱራፌል አንዱ፣ ከመሠዊያው ላይ የእሳት ፍም በጕጠት ወስዶ፣ ወደ እኔ እየበረረ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ከሱራፌል አንዱ፤ ከመሠዊያው ላይ የእሳት ፍም በጉጠት ወስዶ፤ ወደ እኔ እየበረረ መጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሱራፌል አንዱ ወደ እኔ ተላከ፤ በእጁም ከመሠዊያው በጕጠት የወሰደው ፍም ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፥ በእጁም ከመሠዊያው በጕጠት የወሰደው ፍም ነበረ። |
ሱራፌል ተብለው የሚጠሩ መላእክትም በዙሪያው ነበሩ፤ እያንዳንዱ መልአክ ስድስት ክንፍ አለው፤ በሁለቱ ክንፎቹ ፊቱን ይሸፍናል፤ በሁለቱ ክንፎቹ እግሮቹን ሸፍኖ በሁለት ክንፎቹ ይበር ነበር፤
እግዚአብሔርም ቀጭን ሐር የለበሰውን ሰው “ከሕያዋን ፍጥረቶች በታች ባሉት መንኰራኲሮች መካከል አልፈህ ሂድ፤ ከከሰልም ፍም በእጅህ አፍሰህ ውሰድና በከተማይቱ ላይ በትነው!” አለው። እኔም እያየሁት ገባ፤
ከመሠዊያው የሚቃጠል የእሳት ፍም በጥናው ሞልቶም ሁለት እፍኝ ጣፋጭ ሽታ ያለውን የተወቀጠ ደቃቅ ዕጣን በመውሰድ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ያግባ፤
ሙሴም አሮንን እንዲህ አለው፦ “የአንተን ጥና ወስደህ ከመሠዊያው የእሳት ፍም ጨምርበት፤ በፍሙም ላይ ዕጣን አድርግበት፤ ከዚያም ወደ ሕዝቡ በፍጥነት በመሄድ አስተስርይላቸው፤ ፍጠን! እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቊጣ ከመገለጡ የተነሣ በሕዝቡ መካከል መቅሠፍት ጀምሮአል።”
እነሆ፥ እኔ ለንስሓ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤ እርሱ ከእኔ እጅግ ይበልጣል፤ እኔ የእግሩን ጫማ እንኳ ለመሸከም የተገባሁ አይደለሁም።