የተቀበልሻቸው ምክሮች ሁሉ ያደክሙሻል እንጂ ምንም አይጠቅሙሽም፤ በየወሩ መባቻ ከዋክብትን የሚመለከቱ ኮከብ ቈጣሪዎችሽ ወደፊት ይምጡ፤ በአንቺ ላይ ከሚደርሰውም ችግር ያድኑሽ።
ኢሳይያስ 57:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብዙ መንከራተታችሁ የተነሣ ትደክማላችሁ፤ ሆኖም ግን ፍላጎታችሁ በጣም ስለ ተነሣሣ “ጠቃሚ አይደለም” ብላችሁ አላቆማችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንገድ ብዛት ደከምሽ፤ ነገር ግን ‘ተስፋ የለውም’ አላልሽም፤ የጕልበት መታደስ አገኘሽ፤ ስለዚህም አልዛልሽም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፥ ነገር ግን፦ ተስፋ የለም አላልሽም፤ የጉልበትን መታደስ አገኘሽ፥ ስለዚህም አልዛልሽም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፤ ዳግመኛም ጕልበት እያለኝ ከእንግዲህ ወዲህ ይህን መንገድ አልተውም አላልሽም፤ ይህንም ስላደረግሽ አላፈርሽም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፥ ነገር ግን፦ ተስፋ የለም አላልሽም፥ የጕልበትን መታደስ አገኘሽ፥ ስለዚህም አልዛልሽም። |
የተቀበልሻቸው ምክሮች ሁሉ ያደክሙሻል እንጂ ምንም አይጠቅሙሽም፤ በየወሩ መባቻ ከዋክብትን የሚመለከቱ ኮከብ ቈጣሪዎችሽ ወደፊት ይምጡ፤ በአንቺ ላይ ከሚደርሰውም ችግር ያድኑሽ።
እነርሱም ‘ስለምን ብለን ይህን እናደርጋለን? እንዲያውም ያቀድነውን ሁሉ በመፈጸም ከምንጊዜውም ይልቅ እልኸኞችና ዐመፀኞች መሆን እንችላለን’ ብለው ይመልሱልሃል።”
እስራኤል ሆይ! ከሌሎች አማልክት ጋር ለማመንዘር በየስፍራው በመዞር ጫማሽን አትጨርሺ፤ ጉሮሮሽም በውሃ ጥም አይድረቅ፤ አንቺ ግን ‘እኔ ባዕዳን አማልክትን ስለ ወደድኩና እነርሱን ለመከተል ስለ ቈረጥኩ ወደ ኋላ አልመለስም!’ ” ብለሻል።
ወደ ባዕዳን ሕዝብ አማልክት ዘወር በማለትሽ ራስሽን አቃለሻል፤ ከዚህ በፊት በአሦር ምክንያት ኀፍረት እንደ ደረሰብሽ አሁን ደግሞ በግብጽ ምክንያት ኀፍረት ይደርስብሻል።
የበልጉም ሆነ የክረምት ዝናብ ሊቀር የቻለው በዚህ ምክንያት ነው፤ አንቺ ዐይነ ዐፋርነትን አስወግደሽ እንደ አመንዝራ ሴት ኀፍረተቢስ ሆነሻል።
እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።
ሁሉም ባልንጀራውን በማሞኘት ያሳስታል፤ እውነት የሚናገርም የለም፤ አንደበታቸው ውሸት መናገርን እንዲለማመድ አድርገውታል፤ ኃጢአት በመሥራት ሰውነታቸውን ያደክማሉ።