በሁሉም ነገር የተመቻቸና አስተማማኝ፥ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ከእኔ ጋር ስለ ገባ፥ በውኑ ቤቴ ለእግዚአብሔር ታማኝ አይደለም? ርዳታዬና ፍላጎቴስ ሁሉ እንዲሟላ አያደርግምን?
ኢሳይያስ 56:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰንበቴን ለሚያከብሩ፥ እኔ የምፈቅደውን ነገር ለሚመርጡና፥ በቃል ኪዳኔ ለሚጸኑ ጃንደረቦች አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰንበቶቼን ለሚያከብሩ ጃንደረቦች፣ ደስ የሚያሠኘኝን ለሚመርጡ፣ ቃል ኪዳኔን፣ ለሚጠብቁ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰንበቴን ለሚጠብቁ፥ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ለሚመርጡ፥ ቃል ኪዳኔንም ለሚይዙ ጃንደረቦች፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ለጃንደረቦች እንዲህ ይላል፥ “ሰንበቴን ቢጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ቢመርጡ፥ በቃል ኪዳኔም ጸንተው ቢኖሩ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ |
በሁሉም ነገር የተመቻቸና አስተማማኝ፥ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ከእኔ ጋር ስለ ገባ፥ በውኑ ቤቴ ለእግዚአብሔር ታማኝ አይደለም? ርዳታዬና ፍላጎቴስ ሁሉ እንዲሟላ አያደርግምን?
“ጆሮአችሁን አዘንብላችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ቃሌን አድምጡ፤ ዳዊትን እንደ ወደድኩት እናንተን በታማኝነት ለመውደድ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ።
ከባዕድ አገር መጥተው፥ ወደ እግዚአብሔር በመጠጋት እርሱን የሚወዱትንና የሚያገለግሉትን፥ የእርሱን ሰንበት ሳይሽሩ በማክበር ቃል ኪዳኑን የሚጠብቁትን ባዕዳንን እግዚአብሔር እንዲህ ይላቸዋል፦
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በተቀደሰው ቀኔ የራሳችሁን ጥቅም በማሳደድ ሰንበቴን ከመሻር ብትቈጠቡ፥ ሰንበቴን አስደሳች፥ የተከበረውንም የእኔን የእግዚአብሔርን ቀን የተከበረ ቀን ብትሉት፥ የግል ፍላጎታችሁንና የግል ጉዳያችሁን ተግባራዊ ለማድረግ በራሳችሁ አካሄድ መመራትን ትታችሁ ሰንበቴን ብታከብሩ፥
ወደ ጽዮን የሚያደርሰውን መንገድ ይጠይቃሉ፤ አቅጣጫውንም ተከትለው ይጓዛሉ፤ ከእኔም ጋር ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፤ ከቶም አያፈርሱትም።
እርሱን ማምለክ መልካም መስሎ ካልታያችሁ ግን የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በነበሩበት ጊዜ ያመልኩአቸው የነበሩትን ወይም አሁን በምድራቸው የምትኖሩባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደሆን የምታመልኩትን ዛሬውኑ ምረጡ፤ እኔና ቤተሰቤ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።”