ኢሳይያስ 48:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ምድርን መሠረትኩ፤ ሰማያትንም ዘረጋሁ። ስጠራቸውም ይገኛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድርን የመሠረተች የእኔው እጅ ናት፤ ሰማያትን የዘረጋችም ቀኝ እጄ ናት፤ በምጠራቸው ጊዜ፣ ሁሉም በአንድነት ይቆማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች፤ በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጄም ምድርን መሥርታለች፤ ቀኜም ሰማያትን አጽንታለች፤ እጠራቸዋለሁ፤ በአንድነትም መጥተው ይቆማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች፥ በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ። |
በስድስት ቀን እግዚአብሔር ሰማይን፥ ምድርን፥ ባሕርንና በእነርሱ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም።
ውቅያኖስን በእፍኙ፥ ሰማይንም በስንዝሩ፥ የምድርን ዐፈር በቊና መለካት የሚችል ማን ነው? ተራራዎችንና ኰረብቶችንስ በሚዛን የሚመዝን ማን ነው?
እግዚአብሔር ከምድር ክበብ በላይ ዙፋኑን ዘርግቶ መቀመጡን ሰማይን እንደ መጋረጃ መወጠሩንና፥ እንደ መኖሪያ ድንኳን መዘርጋቱን የምድርም ሕዝቦች እንደ ፌንጣ አነስተኞች መሆናቸውን።
ቀና ብላችሁ ወደ ሰማይ ተመልከቱ፤ የምታዩአቸውን ከዋክብት የፈጠረ ማን ነው? እርሱ እንደ ጦር ሠራዊት ይመራቸዋል፤ ምን ያኽል እንደ ሆኑም ቊጥራቸውን ያውቃል፤ እያንዳንዱንም በስሙ ይጠራዋል፤ የእርሱ ሥልጣንና ኀይል እጅግ ታላቅ ነው፤ ስለዚህ ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይጠፋም።
ሰማይን የፈጠረና ከዳር እስከ ዳር የዘረጋው፥ ምድርንና በውስጥዋ የሚኖሩትን ሁሉ የሠራ፥ ሕይወትንና እስትንፋስንም የሰጣቸው፥ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፦
በእናትህ ማሕፀን የፈጠረህ አዳኝህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሁሉን ነገር የፈጠርኩ፥ ሰማያትን ብቻዬን የዘረጋሁ፥ ምድርንም ብቻዬን ያነጠፍኩ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
ምድርን የፈጠርኩና ሰውንም ፈጥሬ በእርስዋ እንዲኖር ያደረግኹ እኔ ነኝ፤ ሰማያትን በኀይሌ የዘረጋሁና ሠራዊቶቻቸውን የምቈጣጠር እኔ ነኝ።”
ሰማያትን የፈጠረው እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ለምድር ቅርጽ ሰጥቶ የሠራት፥ የመሠረታትም እርሱ ነው፤ የፈጠራትም መኖሪያ እንድትሆን ነው እንጂ፥ ቅርጽ የሌላትና ባዶ እንድትሆን አይደለም፤ እርሱ፦ “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤
ምድርን የመሠረተና ሰማያትን የዘረጋ ፈጣሪአችሁን እግዚአብሔርን ረስታችኋል፤ ሊያጠፉአችሁ ከተዘጋጁ ከጨቋኞቻችሁ ቊጣ የተነሣ፥ ዘወትር በፍርሃት ትኖራላችሁ። የእነርሱስ ቊጣ የት አለ?
ስለ አብርሃም፦ “የብዙ ሕዝብ አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ ተጽፎአል፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም የተሰጠው እርሱ የሞቱትን በሚያስነሣውና የሌለውን እንዲኖር በሚያደርገው አምላክ ስለ አመነ ነበር።