ኢሳይያስ 42:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስሜ እግዚአብሔር ነው፤ የእኔንም ክብር የሚጋራ ሌላ አምላክ የለም፤ ጣዖቶችም ምስጋናዬን እንዲካፈሉ አልፈቅድም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜም ይህ ነው! ክብሬን ለሌላ፣ ምስጋናዬንም ለጣዖት አልሰጥም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ጌታ ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ስሜ ይህ ነው፥ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም። |
እግዚአብሔርም “የቀድሞ አባቶቻቸው የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተገለጥኩልህ ለእስራኤላውያን ማስረጃ ይሆን ዘንድ በዚህ ተጠቀም” አለው።
ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ አስቀድሜ ነግሬአችኋለሁ፤ ከመፈጸማቸውም በፊት አስታውቄአችኋለሁ፤ ይህንንም ያደረግኹት ‘ጣዖቶቻችን ይህን አደረጉ፤ የእንጨትና የብረት ምስሎቻችን ይህን ወሰኑ’ እንዳትሉ ነው።
“እኔ የተናገርኩትን ሰምታችኋል፤ ይህም መፈጸሙን አይታችኋል፤ አስተውሉትና እውነተኛነቱን አረጋግጡ፤ ከአሁን ጀምሮ ቀድሞ ተሰውሮ የነበረ እናንተ ያላወቃችሁትን አዲስ ነገር ወደፊት አሳያችኋለሁ።
ይህንንም ያደረገው ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩ፥ እንዲሁም ወልድን እንዲያከብሩ ነው፤ ወልድን የማያከብር፥ ወልድን የላከውን አብን አያከብርም።
“በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግ ቃላት በጥንቃቄ ባትፈጽሙ፥ አስደናቂና አስፈሪ የሆነውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ባታከብሩ፥