ኢሳይያስ 41:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እነዚህ አማልክት ሁሉ ከንቱ ናቸው፤ ምንም ነገር ሊያደርጉ አይችሉም፤ ምስሎቻቸውም እንደ ባዶ ነፋስ ናቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ ሁሉም ከንቱ ናቸው! ሥራቸውም መና ነው፤ ምስሎቻቸውም ባዶ ነፋስ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ እነርሱ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፤ ሥራቸውም ምንም ናት፤ ቀልጠው የተሠሩት ምስሎቻቸውም ባዶ ነፋስ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚሠሩአቸውም በከንቱ ይሠሩአቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ እነርሱ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፥ ሥራቸውም ምንምን ናት፥ ቀልጠው የተሠሩት ምስሎቻቸውም ነፋስና ኢምንት ናቸው። |
ከዚያን በኋላ በገዛ እጃቸው በሠሩት መሠዊያ መታመናቸው ይቀራል፤ እንዲሁም የእጃቸው ሥራ በሆኑት በአሼራ ምስልና ዕጣን ሊያጥኑባቸው በሠሩአቸው መሠዊያዎች መተማመናቸውን ይተዋሉ።
አንሥተውም በትከሻቸው ይሸከሙታል፤ በአንድ ቦታም ሲያኖሩት በዚያው ይቆማል፤ ካለበት ስፍራም መንቀሳቀስ አይችልም። ማንም ሰው ወደ እርሱ ቢጸልይ መልስ አይሰጠውም፤ ወይም ማንንም ከጥፋት ሊያድን አይችልም።
ከአሕዛብ አማልክት መካከል አንዱ እንኳ ዝናብ ማዝነብ አይችልም፤ ሰማይም በራሱ ፈቃድ ካፊያ አያወርድም፤ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ስለ ሆንክ እኛ ተስፋ የምናደርገው በአንተ ነው።
ኧረ ለመሆኑ የጣዖት ጥቅሙ ምንድን ነው? እርሱ እኮ በሰው እጅ ተቀርጾ የተሠራ ነገር ነው፤ ከሐሰት በቀር ከእርሱ ምንም አይገኝም፤ ታዲያ እርሱን ቀርጾ የሠራው ሰው ምንም መናገር በማይችል በዚህ ጣዖት መታመኑ ምን ሊጠቅመው ነው?
ጣዖቶች ዋጋቢስ ነገርን ይናገራሉ፤ ጠንቋዮችም ሐሰተኛ ራእይን ያያሉ፤ የማጭበርበሪያ ሕልምንም ይናገራሉ፤ ስለዚህ ሕዝቡ ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች ይባዝናሉ፤ ማጽናናታቸው ከንቱ ነው፤ ከንቱ የማጽናናት ቃል ይሰጣሉ።
አምስቱም ሰላዮች በቀጥታ ወደ ሚካ ቤት ገብተው ያንን በብር የተለበጠ የእንጨት ጣዖትና ሌሎቹንም ጣዖቶች ኤፉዱንም ጭምር ወሰዱ፤ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ካህኑ የጦር መሣሪያ ከታጠቁት ስድስት መቶ ሰዎች ጋር በቅጽር በሩ አጠገብ ቆሞ ነበር።