አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ዐይናችንን አበራህ፤ እነሆ፥ አሁን ደግሞ ለጥቂት ጊዜ በፊትህ ሞገስን አግኝተን ከእኛ ጥቂቶቹ ከባርነት ቀንበር ነጻ ወጥተው በዚህች ቅድስት ምድር በሰላም ይኖሩ ዘንድ ፈቅደሃል፤ ምንም እንኳ በባርነት አገዛዝ ሥር ብንወድቅም እነሆ አዲስ ሕይወት ሰጥተኸናል።
ኢሳይያስ 22:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እርሱን ኲላብ ተብሎ እንደሚጠራ እንደ ጠንካራ የዕቃ መስቀያ አደርገዋለሁ፤ ለቤተሰቡ ሁሉ የክብር መገኛ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአስተማማኝ ስፍራ እንደ ካስማ እተክለዋለሁ፤ ለአባቱም ቤት የክብር ዙፋን ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአስተማማኝ ስፍራ እንደ ችንካር እተክለዋለሁ፥ ለአባቱም ቤት የክብር ዙፋን ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በታመነ ስፍራ እንደ ችንካር እተክለዋለሁ፤ በአባቱም ቤት የክብር ዙፋን አስቀምጠዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በታመነም ሥፍራ እንደ ችንካር እተክለዋለሁ፥ ለአባቱም ቤት የክብር ዙፋን ይሆናል። |
አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ዐይናችንን አበራህ፤ እነሆ፥ አሁን ደግሞ ለጥቂት ጊዜ በፊትህ ሞገስን አግኝተን ከእኛ ጥቂቶቹ ከባርነት ቀንበር ነጻ ወጥተው በዚህች ቅድስት ምድር በሰላም ይኖሩ ዘንድ ፈቅደሃል፤ ምንም እንኳ በባርነት አገዛዝ ሥር ብንወድቅም እነሆ አዲስ ሕይወት ሰጥተኸናል።
አይሁዳዊው መርዶክዮስ በማዕርግ ደረጃ ከንጉሥ አርጤክስስ ቀጥሎ ሁለተኛ ነበር፤ እርሱም በወገኖቹ በአይሁድ ዘንድ በጣም የተከበረና የተወደደ ሰው ነበር፤ መርዶክዮስ ለወገኖቹና ለዘሮቻቸው በሰላም የመኖር ዋስትና ለማስገኘት በብርቱ የደከመ ሰው ነበር።
እንደዚህ ባለ ጊዜ ችላ ብለሽ ዝም ብትዪ፥ ለአይሁድ ከሌላ ቦታ ርዳታ መምጣቱ አይቀርም፤ እነርሱም በእርግጥ ይድናሉ፤ አንቺ ግን ትሞቻለሽ፤ የአባትሽም የቤተሰብ ሐረግ ተቋርጦ ይቀራል፤ ነገር ግን አንቺ ንግሥት የሆንሽው በዚህ መከራ ጊዜ እኛን ለመታደግ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?”
የጠቢባን ንግግር፥ እረኛ የከብቶቹን መንጋ እንደሚነዳበት ጫፉ እንደ ሾለ በትር ነው፤ በአንድነት የተከማቹ ምሳሌዎች ጠልቀው እንደሚገቡ ምስማሮች ናቸው፤ እነርሱም ከሁላችን ጠባቂ ከእግዚአብሔር የተሰጡ ናቸው።
“ነገር ግን ቤተ ዘመዶቹና የሩቅ ዘመዶቹ የሆኑ ሁሉ እንደ ከባድ ሸክም ይሆኑበታል፤ ከሲኒ አንሥቶ እስከ እንስራ ያሉት የቤት ዕቃዎች ሁሉ በኲላብ ላይ እንደሚሰቀሉ እነርሱም በእርሱ ላይ የሚንጠለጠሉ ይሆናሉ።
በዚያም ቀን የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህ ሁሉ ነገር በሚፈጸምበት ጊዜ ግን ጠንካራው የዕቃ መስቀያ ኲላብ ተነቅሎ ይወድቃል፤ በኲላቡም ላይ ተሰቅሎ የነበረው ዕቃ ሁሉ ተሰባብሮ ይወድቃል።’ ” ይህን የተናገረ እግዚአብሔር ነው።
እርሱ ድኾችን ከትቢያ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ያደርጋቸዋል፤ የክብርም ዙፋን ያወርሳቸዋል የምድርን መሠረቶች የሠራ እግዚአብሔር ነው፤ በእነርሱም ላይ ዓለምን የፈጠረ እርሱ ነው።