ክፉ ሰዎች ቸርነት ብታደርግላቸው እንኳ መልካም መሥራትን አይማሩም፤ በዚህ ጽድቅ በሰፈነበት ምድር እያሉ እንኳ ክፋት ከማድረግ አይቈጠቡም፤ ታላቅነትህንም አይገነዘቡም።
ኢሳይያስ 22:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ግን ጥሪውን በመቀበል ፈንታ በዓል አደረጋችሁ፤ የምትበሉትንም በግና በሬ ዐረዳችሁ፤ ወይን ጠጅም ጠጥታችሁ “ነገ እንሞታለን ዛሬ እንብላ እንጠጣ!” አላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እነሆ፤ ደስታና ሐሤት፣ ፍሪዳ መጣልና ሙክት ማረድ፣ ሥጋ መብላትና የወይን ጠጅ መጠጣት አለ! “ነገ ስለምንሞት፣ እንብላ፤ እንጠጣ!” አላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እናንተ፦ “ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣም” በማለት እነሆም፥ በሐሤትና በደስታ በሬንና በጉንም ስታርዱ፥ ሥጋንም ስትበሉ፥ የወይን ጠጅንም ስትጠጡ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም፥ በዓልን፥ ደስታንና ሐሴትን አደረጋችሁ፤ በሬዎችንና በጎችንም አረዳችሁ፤ “ነገ እንሞታለን፤ እንብላ፤ እንጠጣም፤” እያላችሁ ሥጋን በላችሁ፤ ወይንንም ጠጣችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ ሐሤትና ደስታ በሬንና በጉንም ማረድ ሥጋንም መብላት የወይን ጠጅንም መጠጣት ሆነዋል፥ እናንተ፦ ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣ ብላችኋል። |
ክፉ ሰዎች ቸርነት ብታደርግላቸው እንኳ መልካም መሥራትን አይማሩም፤ በዚህ ጽድቅ በሰፈነበት ምድር እያሉ እንኳ ክፋት ከማድረግ አይቈጠቡም፤ ታላቅነትህንም አይገነዘቡም።
“አንቺ በልብሽ ‘እንደ እኔ ያለ ማንም የለም፤ ባልዋ እንደ ሞተባት ሴት ሆኜ አልኖርም፤ ወይም የልጅ ሞት አይደርስብኝም’ ብለሽ በመዝናናት የተቀመጥሽው ቅምጥሊቱ ሆይ! ይህን ስሚ፦
ሕዝቡም “እነሆ እኛ እንጾማለን፤ አንተ ግን አትመለከተንም፤ የማትመለከተንስ ከሆነ ሰውነታችንን ለምን እናዋርዳለን?” ይላሉ። እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “እነሆ እናንተ በምትጾሙበት ጊዜ የልባችሁን ፈቃድ ትፈጽማላችሁ፤ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ትጨቊናላችሁ፤
የእኅትሽ የሰዶም በደል ይህ ነው፤ እርስዋና መንደሮችዋ ኲራት ተሰምቶአቸው ነበር። የተትረፈረፈ ምግብና የተዝናና ኑሮ ቢኖራቸውም ችግረኞችንና ድኾችን አይረዱም ነበር።
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በየዐውድማው የሚገኘውን የዝሙት ዋጋ ከበዓል የሚሰጥ በረከት መስሎአችሁ፥ ትወዱታላችሁ፤ ይህን በማድረጋችሁ ለአምላካችሁ ታማኞች ሆናችሁ አልተገኛችሁም፤ ስለዚህ እንደ ሌሎች ሕዝቦች መደሰታችሁንና ሐሴት ማድረጋችሁን ተዉ!
እንደ ሰው አስተሳሰብ እኔ በኤፌሶን ከአራዊት ጋር መታገሌ ጥቅሜ ምንድን ነው? ሙታን ከሞት የማይነሡ ከሆነማ “ነገ ስለምንሞት ኑ እንብላ፤ እንጠጣ” እንደ ተባለው መሆኑ ነው።