አንተ ግን ሳትቀበር በእግር እንደሚረጋገጥ የዛፍ ቅጠል የተጣልክ ሆነሃል፤ ሬሳህም በጦርነት ላይ በሞቱ ሰዎች ሬሳ ተሸፍኖአል፤ ከእነርሱም ሬሳ ጋር በድንጋያማ ጒድጓድ ውስጥ ተጥሎ ተረግጦአል።
ኢሳይያስ 18:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወታደሮቻቸው ሬሳ ለወፎችና ለምድረ በዳ አራዊት ምግብ ይሆናል፤ በበጋ ወፎች፥ በክረምትም አራዊት ይቀራመቱታል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉም በተራራ ላይ ለሚኖሩ ነጣቂ አሞሮች፣ ለዱርም አራዊት ይተዋሉ፤ አሞሮች በጋውን ሁሉ ሲበሉት ይባጃሉ፤ የዱር አራዊትም ክረምቱን ሁሉ ሲበሉት ይከርማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተራራ ላይ ላሉ ነጣቂ ወፎች፥ ለምድርም አውሬዎች ይተዋሉ። ነጣቂ ወፎችም በጋውን ሁሉ ይበጁባቸዋል፤ የምድርም አውሬዎች ክረምቱን ሁሉ ሲበሉት ይከርማሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰማይ ወፎችና ለምድር አውሬዎችም በአንድነት ይቀራሉ፤ የሰማይ ወፎችና የምድር አውሬዎችም ሁሉ ይሰበሰቡባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተራራ ላይ ላሉ ነጣቂዎች ወፎች፥ ለምድርም አውሬዎች በአንድነት ይቀራሉ፥ ነጣቂዎችም ወፎች ይበጁባቸዋል፥ የምድርም አውሬዎች ሁሉ ይከርሙባቸዋል። |
አንተ ግን ሳትቀበር በእግር እንደሚረጋገጥ የዛፍ ቅጠል የተጣልክ ሆነሃል፤ ሬሳህም በጦርነት ላይ በሞቱ ሰዎች ሬሳ ተሸፍኖአል፤ ከእነርሱም ሬሳ ጋር በድንጋያማ ጒድጓድ ውስጥ ተጥሎ ተረግጦአል።
እነሆ የባቢሎናውያንን ምድር ተመልከቱ፤ ሕዝቡ ዋጋቢስ ሆኖ ቀርቶአል፤ አሦራውያን ምድሪቱን የአራዊት መፈንጫ አድርገዋታል፤ ምሽጎችዋንም ሰባብረው፥ ምድሪቱን የፍርስራሽ ክምር በማድረግ የራሳቸውን ምሽግ አቁመውባታል።
ከወደ ምሥራቅ እንደ ነጣቂ ጭልፊት ያለውን እጠራለሁ፤ እርሱም ዓላማዬን የሚፈጽም፥ ከሩቅ አገር የሚመጣ ሰው ነው፤ የተናገርኩትን አደርጋለሁ፤ ያቀድኩትንም እፈጽማለሁ።
እኔ እግዚአብሔር አራት ክፉ ነገሮች እንዲደርሱባቸው ወስኛለሁ፤ ስለዚህ በጦርነት ይሞታሉ፤ ሬሳቸውን ውሾች ይጐትቱታል፤ ወፎች ሥጋቸውን ይበሉታል፤ የተረፈውን አራዊት ይግጡታል፤
ሁሉም በአሠቃቂ በሽታ ያልቃሉ፤ የሚያለቅስላቸውም ሆነ የሚቀብራቸው እንኳ አያገኙም፤ ሬሳቸው እንደ ጒድፍ በሜዳ ላይ ይከመራል፤ በጦርነትና በራብ ያልቃሉ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ምግብ ይሆናል።