ኢሳይያስ 14:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀድሞ ስለ ክብርህ በመሰንቆ ይዘመርልህ የነበረው ቆመ፤ አሁን አንተ በትዕቢትህ ወደ ሙታን ዓለም ወረድክ። ስለዚህ አልጋህ ምስጥ፥ ልብስህም የትል መንጋ ሆኖአል።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክብርህ፣ ከነበገና ድምፁ ወደ ሲኦል ወረደ፤ ብሎች ከበታችህ ተነጥፈዋል፤ ትሎችም መደረቢያህ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌጥህና የበገናህ ድምፅ ወደ ሲኦል ወረደ፤ በበታችህም ብል ተነጥፎአል፥ ትልም መደረቢያህ ሆኖአል ብለው ይመልሱልሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከክብርህ ወደ ሲኦል ወደቅህ፤ በበታችህም ብል ተነጥፎአል፤ ትልም መደረቢያህ ሆኖአል” ብለው ይመልሱልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌጥህና የበገናህ ድምፅ ወደ ሲኦል ወረደ፥ በበታችህም ብል ተነጥፎአል፥ ትልም መደረቢያህ ሆኖአል ብለው ይመልሱልሃል። |
እነርሱ ብል እንደ በላው ልብስና ትል እንደበላው ሱፍ ይሆናሉ፤ የእኔ ታዳጊነት ግን ዘለዓለማዊ ነው፤ አዳኝነቴም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል።”
“ወጥተው ሲሄዱም በእኔ ላይ በማመፃቸው የተገደሉትን ሰዎች በድን ያያሉ፤ እነርሱን የሚበላቸው ትል አይሞትም፤ የሚያቃጥላቸውም እሳት አይጠፋም፤ እነርሱንም የሚያያቸው የሰው ዘር ሁሉ ይጸየፋቸዋል።”