ኢሳይያስ 14:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም ይሉታል፥ ‘አንተም ደግሞ እንደኛ ደካማ ሆንክ! ከእኛም እንደ አንዱ ሆንክ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ሁሉ ይመልሱልሃል፤ እንዲህም ይሉሃል፤ “አንተም እንደ እኛ ደከምህ፤ እንደ እኛም ሆንህ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ ሁሉ፦ አንተ ደግሞ እንደ እኛ ደክመሃልን? እኛንስ መስለሃልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ ሁሉ፦ አንተ ደግሞ እንደ እኛ ተይዘሃል፤ እንደ እኛም ተቈጥረሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ ሁሉ፦ አንተ ደግሞ እንደ እኛ ደክመሃልን? እኛንስ መስለሃልን? |
ጥበበኛንም ሆነ ሞኝን ሁለቱንም ለረጅም ጊዜ የሚያስታውሳቸው አይገኝም፤ በሚመጣው ዘመን ሁላችንም የተረሳን ሆነን እንቀራለን፤ ጥበበኞችም ሆንን ሞኞች፥ ሁላችንንም ሞት ይጠብቀናል።
ወደ ሙታን ዓለም ወርደሽ በጥንት ዘመን ይኖሩ ከነበሩ ሕዝቦች ጋር እንድትደባለቂ አደርጋለሁ፤ ከሙታን ጋር ተወዳጅተሽ እንድትኖሪ በዚያ ከምድር በታች ባለ ዓለም ውስጥ ዘለዓለም ፈራርሰው ከቀሩ ነገሮች ጋር እተውሻለሁ፤ ከዚህም የተነሣ ዳግመኛ ሰው አይኖርብሽም፤ በሕያዋንም ምድር ለመኖር ቦታ የለሽም፤
ግብጻውያን ወደ ሙታን ዓለም በሚወርዱበት ጊዜ በሙታን ዓለም ውስጥ የነበሩ ታላላቅ አርበኞች አቀባበል ያደርጉላቸዋል፤ ሲቀበሉአቸውም ‘እናንተ ከተባባሪዎች ጋር ኑ ውረዱ! በጦርነት ከተገደሉት በእግዚአብሔር ከማያምኑ ጋር ተጋደሙ!’ ይሉአቸዋል።