የሠራዊት አምላክ በዚህች በጽዮን ተራራ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤ በግብዣውም ላይ ምርጥ የወይን ጠጅና፥ የተሟላ ምግብ ይዘጋጃል።
ኢሳይያስ 1:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሺ ብላችሁ ብትታዘዙኝ ምድር የምታስገኘውን በረከት ትበላላችሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕሺ ብትሉ፣ ብትታዘዙም የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሺ ብትሉ፤ ብትታዘዙም የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሽ ብትሉና ብትሰሙኝ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ፥ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፥ |
የሠራዊት አምላክ በዚህች በጽዮን ተራራ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤ በግብዣውም ላይ ምርጥ የወይን ጠጅና፥ የተሟላ ምግብ ይዘጋጃል።
በእኔ በእግዚአብሔር ደስ ይላችኋል፤ በምድርም ላይ ከፍ ባለ ቦታ እንድትኖሩ አደርጋለሁ፤ ለቀድሞ አባታችሁ ለያዕቆብ ካወረስኩት ርስት በሚገኘው ምርት እንድትጠግቡ አደርጋችኋለሁ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አገልጋዮቼ ይበላሉ፤ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ አገልጋዮቼ ይጠጣሉ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ አገልጋዮቼ ይደሰታሉ፤ እናንተ ግን ኀፍረት ይደርስባችኋል።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ብዬ እንድናገር አዘዘኝ፦ “እነሆ አድምጡ! እኔ እግዚአብሔር ወደ ሕይወት የሚወስደውንና ወደ ሞት የሚያደርሰውን መንገድ በፊታችሁ አኑሬአለሁ፤ ከሁለቱ አንዱን ምረጡ፤
ብዙ በልታችሁ ትጠግባላችሁ፤ ብዙ አስደናቂ ነገር ያደረግኹላችሁን እኔን እግዚአብሔር አምላካችሁን ታመሰግናላችሁ፤ ሕዝቤ ከእንግዲህ ወዲህ ኀፍረት አይደርስባቸውም።
ሰብላችሁም እጅግ የበዛ ከመሆኑ የተነሣ ገና መከር መሰብሰብ ሳትጨርሱ፥ የወይን ዘለላ የምትቈርጡበት ጊዜ ይደርሳል፤ የወይን ዘለላም ቈርጣችሁ ሳትጨርሱ እህል የምትዘሩበት ወቅት ይደርሳል፤ ለምግብ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ታገኛላችሁ፤ በምድራችሁም በሰላም ትኖራላችሁ።
የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና ሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ተርፈው ከስደት ከተመለሱት ሕዝብ ጋር ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር ቃልና፥ እግዚአብሔር የላከው ስለ ሆነ በነቢዩ ሐጌ አማካይነት ለተላከው መልእክት ታዛዦች ሆኑ፤ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ።
“ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ብትታዘዝና ዛሬ እኔ የምሰጥህንም ትእዛዞች ሁሉ በታማኝነት ብትጠብቅ፥ በምድር ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤