ዕብራውያን 9:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመጀመሪያው ኪዳን የአምልኮ አገልግሎት ሥርዓትና ምድራዊ መቅደስ ነበረው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመጀመሪያው ኪዳን የአምልኮ ሥርዐትና ምድራዊ መቅደስ ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመጀመሪያው ኪዳን የአገልግሎት ሥርዓትና ምድራዊ መቅደስ ነበራት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊተኛይቱም ደግሞ የአገልግሎት ሥርዐትና የዚህ ዓለም የሆነው መቅደስ ነበራት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፊተኛይቱም ደግሞ የአገልግሎት ስርዓትና የዚህ ዓለም የሆነው መቅደስ ነበራት። |
ባደረጉት ነገር ሁሉ የሚያፍሩ ከሆነ ስለ ቤተ መቅደሱ አሠራር ንድፍ፥ ስለ አደረጃጀቱ ስለ መውጫዎቹና ስለ መግቢያዎቹ፥ ስለ አጠቃላይ፥ አሠራሩ ሁኔታ፥ ስለ ሥነ ሥርዓቱ፥ ስለ ሕጎቹ ሁሉ አስረዳቸው፤ አጠቃላይ ንድፉን አጥንተው ሥርዓቱን ሁሉ ተግባራዊ ያደርጉ ዘንድ በእነርሱ ፊት ጻፈው።
“እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዝ ሁሉ ፈጽሙ፤ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ ይፈጽሙት የነበረውን የረከሰ ልማድ አትከተሉ፤ ከእነዚህ አሳፋሪ ተግባሮች አንዱንም በመፈጸም ራሳችሁን አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”
“ካህናት ሁሉ እኔ የሰጠኋቸውን የሥርዓት መመሪያዎች ይጠብቁ፤ ይህን ባያደርጉ ግን ለተቀደሱት የትእዛዝ መመሪያዎች ባለመታዘዛቸው በደል ሆኖባቸው ይሞታሉ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
እስከ ማግስቱ ጠዋት ድረስ ከዚያ ምግብ አስተርፈው አያሳድሩ፤ ከእንስሳውም አጥንት አንዱንም አይስበሩ፤ በተሰጣቸው የሥርዓት መመሪያ መሠረት በዓሉን ያክብሩ፤
እነርሱ እስራኤላውያን ናቸው፤ እግዚአብሔርም እነርሱን ልጆቹ አደረጋቸው፤ ክብሩን ገለጠላቸው፤ ቃል ኪዳን ገባላቸው፤ ሕግን ሰጣቸው፤ እውነተኛውን የአምልኮ ሥርዓት አሳያቸው፤ የተስፋውንም ቃል ሰጣቸው።
በክርስቶስ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በሰው ሠራሽ ወግና በዓለማዊ ተራ ሥርዓት ላይ በተመሠረተ በፍልስፍናና በከንቱ ሽንገላ ማንም እንዳያጠምዳችሁ ተጠንቀቁ።
እንግዲህ “አዲስ ቃል ኪዳን” ሲል የፊተኛውን ቃል ኪዳን አሮጌ አድርጎታል ማለት ነው፤ ስለዚህ የተሠራበትና አሮጌው ነገር ሁሉ የሚጠፋበት ጊዜ ተቃርቧል።
ክርስቶስ የእውነተኛይቱ “መቅደስ” ምሳሌ ወደ ሆነችውና በሰው እጅ ወደተሠራችው ቅድስተ ቅዱሳን አልገባም፤ እርሱ አሁን ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት ወደ ሰማይ ገባ።