ሰዎቹም “በሕግ ተጽፎ የምናገኘው ‘መሲሕ ለዘለዓለም ይኖራል’ የሚል ነው፤ ታዲያ፥ አንተ፥ ‘የሰው ልጅ ወደ ላይ ከፍ ማለት አለበት’ እንዴት ትላለህ? ይህስ የሰው ልጅ ማን ነው?” አሉት።
ዕብራውያን 7:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ግን ለዘለዓለም የሚኖር በመሆኑ ክህነቱ የማይለወጥ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ግን ለዘላለም የሚኖር በመሆኑ፣ ክህነቱ የማይሻር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን ለዘለዓለም ይኖራል፤ ክህነቱ አይሻርምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ |
ሰዎቹም “በሕግ ተጽፎ የምናገኘው ‘መሲሕ ለዘለዓለም ይኖራል’ የሚል ነው፤ ታዲያ፥ አንተ፥ ‘የሰው ልጅ ወደ ላይ ከፍ ማለት አለበት’ እንዴት ትላለህ? ይህስ የሰው ልጅ ማን ነው?” አሉት።
እነርሱ በትውልዳቸው ከነገድ አባቶች የመጡ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የመጣው ከእነርሱ ዘር ነው፤ እርሱ ከሁሉ በላይ ነው፤ ለዘለዓለምም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን!
ሕግ የካህናት አለቆች አድርጎ የሚሾማቸው ደካሞች ሰዎችን ነው፤ ከሕግ በኋላ የመጣው የመሐላ ቃል ግን ለዘለዓለም ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ልጅ ሾሞአል።
ለእኔም እንደ ልቤና እንደ ሐሳቤ የሚያደርግ አንድ ታማኝ ካህን አስነሣለሁ፤ ለእርሱም የጸና ዘር እመሠርትለታለሁ፤ እኔ በቀባሁትም ንጉሥ ፊት ይመላለሳል።