ዕብራውያን 7:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የክህነት ሐረጉ ሲለወጥ ሕጉም አብሮ መለወጥ አለበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክህነት ለውጥ ካለ ሕጉም ሊለወጥ ግድ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም ክህነቱ ሲለወጥ፥ ሕጉ ደግሞ ሊለወጥ ግድ ይላልና ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክህነታቸው ታልፍ ዘንድ አላትና፤ ክህነታቸው ካለፈችም ኦሪታቸው ታልፋለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክህነቱ ሲለወጥ፥ ሕጉ ደግሞ ሊለወጥ የግድ ነውና። |
ታላቅና ታናሽ እኅቶችሽን ወስጄ ለአንቺ እንደ ልጆችሽ አድርጌ በምሰጥበት ጊዜ የቀድሞውን አካሄድሽን አስታውሰሽ ታፍሪአለሽ። ይህ የሚሆነው ግን ከአንቺ ጋር በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት አይደለም።
እንግዲህ ለሕዝቡ ሕግ የተሰጠው በሌዊ ክህነት መሠረት ነው፤ በዚህ በሌዋውያን ክህነት ፍጹምነት ቢገኝ ኖሮ የአሮን የክህነት ሹመት ሳይሆን የመልከ ጼዴቅ የክህነት ሹመት ያለው ሌላ ካህን መምጣት ባላስፈለገም ነበር፤
እነዚህ ነገሮች የመታደስ ጊዜ እስኪመጣ ድረስ በሥራ ላይ የዋሉ አፍአዊ ሥርዓቶች ናቸው፤ እነርሱ ስለ መብልና ስለ መጠጥ፥ ስለ ልዩ ልዩ የመንጻት ሥርዓቶችም ብቻ የተደረጉ ናቸው።