ዕብራውያን 4:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በዚሁ ስፍራ ላይ እንደገና “እኔ ወደምሰጣቸው የዕረፍት ቦታ ከቶ አይገቡም” ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀደም ባለው ክፍል ደግሞ፣ “ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ስፍራም ደግሞ “ወደ ዕረፍቴ አይገቡም፤” ይላል፥፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳግመኛም፥ “ወደ ዕረፍቴ አይገቡም” ብሎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚህ ስፍራም ደግሞ፦ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም። |
የእርሱ ሥራ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተጠናቀቀ ቢሆንም እንኳ፦ “እኔ ወደምሰጣቸው የዕረፍት ቦታ ከቶ አይገቡም ብዬ በቊጣዬ ምዬአለሁ” እንዳለው አሁንም እኛ የምናምነው ወደዚያ እግዚአብሔር ወደሚሰጠን የዕረፍት ቦታ እንገባለን፤