ሐጌ 2:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዓለም የሚገኝ ወርቅና ብር ሁሉ የእኔ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ብሩ የእኔ ነው፤ ወርቁም የእኔ ነው’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብሩ የእኔ ነው፥ ወርቁም የእኔ ነው፥ ይላል የሠራዊት ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብሩ የእኔ ነው፥ ወርቁም የእኔ ነው፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብሩ የእኔ ነው፥ ወርቁም የእኔ ነው፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። |
ቤተ መቅደሴ ያረፈበትን ቦታ ለማስዋብ የሊባኖስ ግርማ የሆኑት ዝግባ አስታና ጥድ ወደ አንቺ እንዲመጡ ይደረጋሉ፤ እኔም የእግሬ ማረፊያ የሆነውን አከብረዋለሁ።
“እኔ በነሐስ ፈንታ ወርቅ፥ በብረት ፈንታ ብር፥ በእንጨት ፈንታ ነሐስ፥ በድንጋይም ፈንታ ብረት አመጣለሁ፤ ሰላምን እንደ አስተዳዳሪሽ ጽድቅንም እንደ ገዢሽ አድርጌ እመድባለሁ።