ዕንባቆም 3:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀስትህን ከሰገባው አወጣህ፤ ፍላጻህንም ለመወርወር አነጣጠርህ፤ ምድሪቱንም ሰንጥቀህ ወንዞች አስገኘህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀስትህን አዘጋጀህ፤ ፍላጻም እንዲመጣልህ አዘዝህ፤ ሴላ ምድርን በወንዞች ከፈልህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀስትህን ገለጥህ በቃልህ እንደ ማልህ መቅሠፍትህን አወጣህ፤ ቀስትህንም ገተርህ፤ ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቃልህ እንደ ማልህ መቅሠፍትህን አወጣህ፣ ቀስትህንም ገተርህ፣ ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቃልህ እንደ ማልህ መቅሠፍትህን አወጣህ፥ ቀስትህንም ገተርህ፥ ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ። |
እነሆ፥ እኔ በሲና ተራራ በአለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ አንተም አለቱን ምታው፤ ሕዝቡም የሚጠጡት ውሃ ከውስጡ ይፈልቃል፤” ሙሴም በእስራኤል አለቆች ፊት እንደዚሁ አደረገ።
እንደ ጠላት ቀስቱን ገተረ፤ በቀኝ እጁ የያዘውን በእኛ ላይ አነጣጠረ፤ በኢየሩሳሌም ከተማ የምንመካባቸውን ሁሉ ገደለ፤ ቊጣውንም እንደ እሳት አቀጣጠለ።
ሁሉም አንድ ዐይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ የጠጡትም ይከተላቸው ከነበረው ከዚያ ከመንፈሳዊ አለት የመነጨ ነበር፤ ያም አለት ራሱ ክርስቶስ ነበር።