ንጉሡም የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ ሙሴን ለማስገደል ፈለገ፤ ሙሴ ግን ኰብልሎ በዚያው ለመኖር ወደ ምድያም አገር ሄደ። እዚያም እንደ ደረሰ በውሃ ጒድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤
ዕንባቆም 3:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢትዮጵያ ሰፈር ሲጨነቅ፥ የምድያምም ሰዎች ሲንቀጠቀጡ አየሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ፣ የምድያምም መኖሪያዎች ሲታወኩ አየሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኢትዮጵያ ድንኳኖች በጭንቀት ላይ ሆነው አየሁ፥ የሚድያን ምድር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፣ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፥ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ። |
ንጉሡም የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ ሙሴን ለማስገደል ፈለገ፤ ሙሴ ግን ኰብልሎ በዚያው ለመኖር ወደ ምድያም አገር ሄደ። እዚያም እንደ ደረሰ በውሃ ጒድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤
ድንኳኖቻቸውን፥ መንጋዎቻቸውን፥ መጋረጃዎቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን ሁሉ ውሰዱ፤ ግመሎቻቸውን ለራሳችሁ ውሰዱ። ‘በዙሪያው ሽብር ተነሥቷል’ ብለው ይጮኻሉ።”
ግብጽን ለቃችሁ በወጣችሁ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ቀይ ባሕርን በፊታችሁ እንዴት እንዳደረቀ ሰምተናል፤ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ የነበሩትን ሁለቱን የአሞራውያን ነገሥታት ሲሖንንና ዖግን እንዴት እንደ ገደላችሁም ሰምተናል።
እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “ጌታችን ሆይ! እኛ አገልጋዮችህ በእርግጥ ይህን አድርገናል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር እናንተ በውስጧ የሚኖሩትን ሕዝብ በመግደል ምድሪቱን ያወርሳችሁ ዘንድ አገልጋዩን ሙሴን ያዘዘው መሆኑን ዐውቀናል፤ ይህንንም ያደረግነው እናንተን ከመፍራታችን የተነሣ ሕይወታችንን ለማትረፍ ፈልገን ነው።
ሁለቱ የምድያማውያን ነገሥታት ዜባሕና ጻልሙናዕ ሸሹ፤ ነገር ግን ጌዴዎን አሳዶ ማረካቸው፤ ሠራዊታቸውንም በሙሉ በድንጋጤ ላይ እንዲወድቁ አደረገ።