ዘፍጥረት 9:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኖኅ ገበሬ ነበረ፤ የወይን ተክልንም መትከል ጀመረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኖኅ ገበሬ ነበረና ወይን ተከለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኖኅ ቀዳሚ ገበሬ ነበረ፤ የወይን ተክልንም ተከለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፤ ወይንም ተከለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፥ ወይንም ተከለ። |
መልኬን ያጠቈረው የፀሐይ ቃጠሎ ነው፤ ስለዚህ ጥቊር በመሆኔ አትናቁኝ፤ የእናቴ ልጆች የሆኑ ወንድሞቼ ስለ ተጣሉኝ የወይን ተክል ጠባቂ አደረጉኝ፤ ስለዚህ የግሌ የወይን ተክል ለመጠበቅ ጊዜ አልነበረኝም።
ያለ ደመወዝ በራሱ ገንዘብ በወታደርነት የሚያገለግል ማነው? ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላስ ማነው? መንጋ እየጠበቀ የመንጋውን ወተት የማይጠጣ ማን ነው?
ወይስ አዲስ የወይን ተክል ተክሎ የመጀመሪያውን ፍሬ ያልሰበሰበ ሰው ይገኛልን? ይህ ከሆነ እርሱ ወደ ቤቱ ይመለስ፤ እርሱ በጦርነት ላይ ቢሞት ወይን ጠጁ ለሌላ ሰው መደሰቻ ይሆናል።
“ልጃገረድ ለማግባት ታጫለህ፤ ነገር ግን ሌላ ሰው ይደፍራታል፤ ቤት ትሠራለህ፤ ነገር ግን አትኖርበትም፤ ወይን ትተክላለህ፤ ነገር ግን በፍሬው አትጠቀምበትም።