ዘፍጥረት 8:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰባተኛው ወር፥ በዐሥራ ሰባተኛው ቀን መርከቡ “አራራት” ከተባሉት ተራራዎች በአንደኛው ጫፍ ላይ ዐረፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰባተኛው ወር፣ በዐሥራ ሰባተኛው ቀን መርከቧ በአራራት ተራሮች ላይ ዐረፈች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መርከቢቱም በሰባተኛው ወር፥ ከወሩም በዓሥራ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች በአንደኛው ጫፍ ላይ ዐረፈች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መርከቢቱም በሰባተኛው ወር ከወሩም በሃያ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች ላይ ተቀመጠች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መርከቢቱም በስባተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች፤ ላይ ተቀመጠች። |
ከዕለታት በአንዱ ቀን ኒስሮክ በሚል ስም በሚጠራው ባዕድ አምላኩ ቤተ መቅደስ ውስጥ በስግደት ላይ እንዳለ፥ ከልጆቹ ሁለቱ በተለይ አድራሜሌክና ሣሬጼር ተብለው የሚጠሩት በሰይፍ ገደሉት፤ እነርሱም ወደ አራራት አምልጠው ሄዱ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ከልጆቹ አንዱ አስራዶ የተባለው ነገሠ።
ከዕለታት በአንዱ ቀን ኒሰሮክ በሚል ስም በሚጠራው ጣዖት ቤተ መቅደስ ውስጥ በስግደት ላይ እንዳለ ከልጆቹ ሁለቱ በተለይ አድራሜሌክና ሣሬጼር ተብለው የሚጠሩት በሰይፍ ገደሉት፤ እነርሱም ወደ አራራት አምልጠው ሄዱ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ከልጆቹ አንዱ አስራዶን የተባለው ነገሠ።
“አደጋ ለመጣል የሚያስችል ምልክት ስጡ! ሕዝቦች ሁሉ መስማት እንዲችሉ እምቢልታ ንፉ! ባቢሎንን ይወጉ ዘንድ ሕዝቦችን አዘጋጁ! የአራራት፥ የሚኒና የአሽኬናዝ መንግሥታት አደጋ እንዲጥሉ ንገሩአቸው፤ የጦር አዛዥ የሚሆን ሰው ሹሙ፤ ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ፈረሶችን አምጡ።