ዘፍጥረት 7:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዝናብም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዘነበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ ዘነበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዝናቡም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዘነበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዝናቡም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰማይም መስኮቶች ተከፈቱ ዝናቡም አርባ ቀንም አርባ ሌሊት በምድት ላይ ሆነ። |
ኤልያስም ተነሥቶ ምግቡን በላ፥ ውሃውንም ጠጣ፤ ከዚያም ምግብ ባገኘው ኀይል እስከ ተቀደሰው የሲና ተራራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ተጓዘ፤
“እኔም ከዚህ በፊት ባደረግሁት ዐይነት እንደገና በተራራው ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በመጸለይ ቈየሁ፤ እግዚአብሔርም እንደገና ልመናዬን ሰምቶ አንተን ላለማጥፋት ፈቀደ።
ከዚህም በኋላ እንደገና አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ምንም ነገር ሳልበላና ሳልጠጣ በእግዚአብሔር ፊት በግንባሬ ተደፍቼ ቈየሁ። ይህንንም ያደረግኹት እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ኃጢአት ሠርታችሁ እርሱን በማስቈጣታችሁ ምክንያት ነበር።
እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባው ቃል ኪዳን የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላቶች ለመቀበል እኔ ወደ ተራራው ወጥቼ ነበር፤ በዚያም ምንም ነገር ሳልበላና ሳልጠጣ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቈየሁ።