ዘፍጥረት 45:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሴፍ ወንድሞች ከግብጽ ተነሥተው በከነዓን ወደሚኖረው አባታቸው ወደ ያዕቆብ ተመለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ከግብጽ ወጥተው በከነዓን ምድር ወደሚኖረው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ከግብጽ አገርም ወጡ፥ ወደ ከነዓንም ምድር ከአባታቸው ከያዕቆብ ዘንድ ደረሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ከግብፅ ሀገር ወጥተው ሄዱ፤ ወደ ከነዓንም ምድር ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ ደረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ሄዱ ከግብፅ አገርም ወጡ ወደ ከነዓንም ምድር ከአባታቸው ከያዕቆብም ዘንድ ደረሱ። |
እዚያም እንደ ደረሱ አባታቸውን “ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በመላው ግብጽ ላይ አስተዳዳሪ ሆኖአል” አሉት። ያዕቆብ ግን እጅግ ደነገጠ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም።