ዘፍጥረት 45:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያዕቆብ ልጆች ልክ እንደ ተነገራቸው አደረጉ፤ ዮሴፍም በንጉሡ ትእዛዝ መሠረት ሠረገሎችንና ለጒዞ የሚሆናቸውን ስንቅ ሰጣቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤልም ልጆች ይህንኑ አደረጉ። ዮሴፍም ፈርዖን ባዘዘው መሠረት ሠረገላዎች አቀረበላቸው፤ የመንገድም ስንቅ አስያዛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ልጆችም እንደተነገራቸው አደረጉ፤ ዮሴፍም በፈርዖን ትእዛዝ ሰረገሎችንና ለመንገድ ስንቅ ሰጣቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ልጆችም እንደ አዘዛቸው አደረጉ፤ ዮሴፍም የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን እንደ ነገረው ሰረገሎችንና ለመንገድ ስንቅን ሰጣቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ልጆችም እንደዚሁ አደረጉ ዮሴፍም በፈርዖን ትእዛዝ ሰረገሎችንና |
ነገር ግን ዮሴፍ ያላቸውን ሁሉ በነገሩት ጊዜና እርሱን ወደ ግብጽ የሚወስዱበትን ዮሴፍ የላከለትን ሠረገላ ባየ ጊዜ ሕይወቱ በደስታ ታደሰ፤
ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሥቶ ወደ ግብጽ ጒዞ ጀመረ፤ ልጆቹም አባታቸውን ያዕቆብን፥ ሕፃናት ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን የግብጽ ንጉሥ በላካቸው ሠረገሎች አሳፍረው፥
በዚህም ዐይነት ለእግዚአብሔር የሚቀርበው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት፥ የፋሲካ በዓል አከባበርና የሚቃጠለውን መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ የማቅረቡ ሥራ ሁሉ ንጉሥ ኢዮስያስ ባዘዘው መሠረት በዚያ ቀን ተከናወነ።
ሙሴ ባዘዘው መሠረትም በእያንዳንዱ የበዓል ቀን ማለትም በየሰንበቱ፥ በየወሩ መባቻ፥ በየዓመቱ በሚከበሩ ሦስት በዓላት ማለትም በቂጣ በዓል፥ በመከር በዓልና በዳስ በዓል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀርብ ነበር።
መላው የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር “ሲን” ተብሎ የሚጠራውን ምድረ በዳ ትተው በረፊዲም ሰፈሩ፤ ነገር ግን በዚያ የሚጠጣ ውሃ አልነበረም።
“በትእዛዙ ላይ ያመፅሁ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔር ባደረገው ነገር እውነተኛ ነው፤ እናንተ ሕዝቦች ሁሉ አድምጡ ሥቃዬንም ተመልከቱ፤ ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ተማርከው ተወስደዋል።
እነርሱም በብዙ ሠረገላና ስንቅ በተጫኑ ጋሪዎች የተጠናከረ ታላቅ ሠራዊት መርተው በማምጣት በሁሉም አቅጣጫ አደጋ ይጥሉብሻል፤ በጋሻና በራስ ቊር እየተከላከሉ ይከቡሻል፤ እኔም ለእነርሱ ፍርድ አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ እነርሱም በራሳቸው ሕግ መሠረት ይቀጡሻል።