ከከተማው ወጥተው ገና ጥቂት መንገድ ርቀው እንደ ሄዱ፥ ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ አለው፤ “እነዚያን ሰዎች ተከታትለህ ያዛቸው፤ ወደ እነርሱም ስትደርስ ‘በመልካም ፈንታ ክፉ የመለሳችሁት ስለምንድን ነው?
ዘፍጥረት 44:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድማማቾቹ ይህን ባዩ ጊዜ በሐዘን ልብሶቻቸውን ቀደዱ፤ ስልቻዎቻቸውንም ጭነው ወደ ከተማ ተመለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ልብሳቸውን በሐዘን ቀደዱ፤ ሁሉም ስልቾቻቸውን በየአህዮቻቸው ጭነው ወደ ከተማዪቱ ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ ልብሳቸውን በኀዘን ቀደዱ፤ ሁሉም ስልቾቻቸውን በየአህዮቻቸው ጭነው ወደ ከተማዪቱ ተመለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልብሳቸውንም ቀደዱ፤ ዓይበታቸውንም በየአህዮቻቸው ጭነው ወደ ከተማዪቱ ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልብሳቸውንም ቀደዱ ዓይበታቸውንም በየአህዮቻቸው ጭነው ወደ ከተማይቱ ተመለሱ። |
ከከተማው ወጥተው ገና ጥቂት መንገድ ርቀው እንደ ሄዱ፥ ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ አለው፤ “እነዚያን ሰዎች ተከታትለህ ያዛቸው፤ ወደ እነርሱም ስትደርስ ‘በመልካም ፈንታ ክፉ የመለሳችሁት ስለምንድን ነው?
በሦስተኛው ቀን አንድ ወጣት ከሳኦል ሰፈር መጣ፤ ልብሱን ቀዶ በራሱ ላይ ትቢያ ነስንሶ ነበር፤ ወደ ዳዊትም ቀርቦ በአክብሮት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፤
እዚያም እንደ ደረሰች አዲሱ ንጉሥ በተለመደው ባህል መሠረት በቤተ መቅደሱ መግቢያ በሚገኘው ዐምድ አጠገብ ቆሞ አየችው፤ እርሱም በጦር አዛዦችና በእምቢልታ ነፊዎች ታጅቦ ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ በደስታ ተሞልተው እልል እያሉ እምቢልታ ይነፉ ነበር፤ ዐታልያም በድንጋጤ ልብስዋን ቀዳ “ይህ በክሕደት የተፈጸመ ሤራ ነው! ሤራ ነው!” ስትል ጮኸች።