ዮሴፍ ብንያምን ከእነርሱ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ ጠራውና “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ውሰዳቸው፤ ዛሬ ቀን ከእኔ ጋር ምሳ ስለሚበሉ አንድ ከብት ዕረድና አዘጋጅ” አለው።
ዘፍጥረት 43:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዛዡም ዮሴፍ በነገረው መሠረት ሰዎቹን ወስዶ ወደ ቤት አስገባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዛዡም ዮሴፍ የነገረውን አደረገ፤ ሰዎቹንም ወደ ዮሴፍ ቤት ወሰዳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዛዡም ዮሴፍ የነገረውን አደረገ፤ ሰዎቹንም ወደ ዮሴፍ ቤት ወሰዳቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ሰው ዮሴፍ እንዳለው አደረገ፤ ሰዎቹንም ወደ ዮሴፍ ቤት አስገባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያ ስውም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ ያ ሰውም ስዎቹን ወደ ዮሴፍ ቤት አስገባ። |
ዮሴፍ ብንያምን ከእነርሱ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ ጠራውና “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ውሰዳቸው፤ ዛሬ ቀን ከእኔ ጋር ምሳ ስለሚበሉ አንድ ከብት ዕረድና አዘጋጅ” አለው።
“ወደ እዚህ ያመጡን በመጀመሪያ ጊዜ በስልቻዎቻችን ውስጥ ተመልሶ ስለ ተገኘው ገንዘብ ሳይሆን አይቀርም” በማለት፤ ሰዎቹ ወደ ዮሴፍ ቤት በሚሄዱበት ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ “በዚህ ምክንያት ያሠቃዩናል፤ አህዮቻችንን ወስደው እኛንም የእነርሱ ባሪያዎች ያደርጉናል” ብለውም አሰቡ።