ዘፍጥረት 42:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍ ወንድሞቹን ባያቸው ጊዜ ዐወቃቸው፤ ነገር ግን የማያውቃቸው በመምሰል በቊጣ ቃል “ከየት ነው የመጣችሁት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም “እህል ለመሸመት ከከነዓን አገር መጣን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍም ወንድሞቹን ገና ሲያያቸው ወዲያውኑ ዐወቃቸው፤ ነገር ግን እንደማያውቃቸው ሆኖ፣ “ከየት የመጣችሁ ናችሁ?” ብሎ በቍጣ ቃል ተናገራቸው። እነርሱም፣ “እህል ለመሸመት ከከነዓን ምድር የመጣን ነን” ብለው መለሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም ወንድሞቹን ገና ሲያያቸው ወዲያውኑ ዐወቃቸው፤ ነገር ግን እንደማያውቃቸው ሆኖ፥ “ከየት የመጣችሁ ናችሁ?” ብሎ በቁጣ ቃል ተናገራቸው። እነርሱም፥ “እህል፤ ለመሸመት ከከነዓን ምድር የመጣን ነን” ብለው መለሱለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም ወንድሞቹን በአያቸው ጊዜ ዐወቃቸው፤ እንደማያውቃቸውም ሆነ፤ ክፉ ቃልንም ተናገራቸው፥ “እናንተ ከወዴት መጣችሁ?” አላቸው። እነርሱም፥ “ከከነዓን ምድር እህል ልንሸምት የመጣን ነን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም ወንድሞቹን አይቶ አወቃቸው ተለወጠባቸውም ክፋ ቃልንም ተናገራቸው፦ እናንተ ከወዴት መጣችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ ከከነዓን ምድር እህል ልንሸምት የመጣን ነን አሉት። |
ወንድማማቾቹ ከታላቁ አንሥቶ እስከ ታናሹ በዕድሜ ተራ በዮሴፍ ፊት ለፊት ተቀመጡ፤ እንዴት እንደ ተቀመጡ ባዩ ጊዜ በመደነቅ እርስ በርሳቸው ተያዩ።