ዘፍጥረት 42:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ የአንድ ሰው ልጆች የሆንን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ አንዱ ጠፍቶአል፤ የመጨረሻ ታናሽ ወንድማችን በከነዓን ከአባታችን ጋር አለ’ አልነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ የአንድ አባት ልጆች የሆንን፣ ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ አንዱ የለም፤ ታናሽ ወንድማችን ግን ከአባታችን ጋራ በከነዓን ይገኛል።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ የአንድ አባት ልጆች የሆን፥ ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ አንዱ የለም፤ ታናሽ ወንድማችን ግን ከአባታችን ጋር በከነዓን ይገኛል።’” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ የአባታችን ልጆች ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ አንዱ ሞቶአል፤ ታናሹም በከነዓን ምድር ዛሬ ከአባታችን ጋር አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ የአባታችን ልጆች አሥራ ሁለት ወንድማማች ነን አንዱ ጠፍቶአል ታናሹም በከነዓን ምድር ዛሬ ከአባታችን ጋር አለ። |
እነርሱም “እኛ አገልጋዮችህ በከነዓን ምድር የሚኖር የአንድ ሰው ልጆች የሆንን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ አንዱ ወንድማችን ሞቶአል፤ የመጨረሻ ታናሽ ወንድማችን አሁን ከአባታችን ጋር ይገኛል” አሉት።
ሰውየውም እንዲህ አለን፤ ‘ታማኞች ሰዎች መሆናችሁን የማውቀው ይህን አንድ ነገር ብታደርጉ ነው፤ ይኸውም ከእናንተ አንዱ ከእኔ ጋር ይቈይ፤ ሌሎቻችሁ ለተራቡት ቤተሰቦቻችሁ እህል ይዛችሁ ወደ አገራችሁ ተመለሱ፤
በመጀመሪያ በቊጥር ትንሽ የሆነው የብንያም ነገድ ታየ፤ ቀጥሎም የይሁዳ መሪዎች ከነጭፍሮቻቸው ታዩ። በመጨረሻም የዛብሎንና የንፍታሌም መሪዎች ተከተሉ።