ዘፍጥረት 42:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሴፍ ወንድሞች የገዙትን እህል በአህዮቻቸው ጭነው ጒዞ ጀመሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እህላቸውን በአህዮቻቸው ጭነው ጕዟቸውን ቀጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እህላቸውን በአህዮቻቸው ጭነው ጉዞአቸውን ቀጠሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም እህሉን በአህዮቻቸው ላይ ጫኑ፤ ከዚያም ተነሥተው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም እህሉን በአህዮቻቸው ላይ ጫኑ ከዚያም ተነሥተው ሄዱ። |
ከዚህ በኋላ ታናሽ ወንድማችሁን ይዛችሁልኝ ኑ፤ በዚህ ዐይነት የተናገራችሁት ሁሉ እውነት መሆኑ ይረጋገጣል፤ ከመሞትም ትድናላችሁ።” እነርሱም በዚህ ነገር ተስማሙ፤
ዮሴፍ አገልጋዮቹን “ለእነዚህ ሰዎች በየስልቻዎቻቸው እህል ሙሉላቸው፤ ገንዘባቸውንም መልሳችሁ በየስልቻዎቻቸው ውስጥ ቋጥሩላቸው፤ ለጒዞአቸውም ስንቅ አስይዙአቸው” ብሎ አዘዘ። ይህም ከተደረገላቸው በኋላ፥
በመንገድ ላይ ሳሉ ለዐዳር በሰፈሩበት ቦታ ከእነርሱ አንዱ ለአህያው ጥሬ ለመስጠት ስልቻውን በፈታ ጊዜ በስልቻው አፍ ላይ ገንዘቡ ተቋጥሮ አገኘው።