ዘፍጥረት 42:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኛ ሁላችን የአንድ ሰው ልጆች ነን፤ እኛ የምንታመን ነን፤ ሰላዮችም አይደለንም” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁላችንም የአንድ አባት ልጆች ነን፤ አገልጋዮችህ የታመንን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አይደለንም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁላችንም የአንድ አባት ልጆች ነን፤ አገልጋዮችህ የታመንን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አይደለንም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ ሁላችን የአንድ ሰው ልጆች ነን፤ እኛ የሰላም ሰዎች ነን፤ ባሪያዎችህስ ሰላዮች አይደሉም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እና ሁላችን የአንድ ሰው ልጆች ነን እኛ እውነተኞች ነን ባሪያዎችህስ ሰላዩች አይደሉም |
ከእናንተ አንዱ ሄዶ ወንድማችሁን ያምጣ፤ የተናገራችሁት እውነት መሆኑ ተረጋግጦ ነጻ እስክትለቀቁ ድረስ የቀራችሁት እዚሁ በእስር ቤት ትቈያላችሁ አለበለዚያ ግን በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ እናንተ ሰላዮች ናችሁ።”
እነርሱም “ሰውየው ስለ ራሳችንና ስለ ቤተሰባችን አጥብቆ መረመረን፤ ‘አባታችሁ በሕይወት አለን? ሌላስ ወንድም አላችሁን?’ ብሎ ጠየቀን፤ እኛም ለጥያቄው ተገቢውን መልስ ሰጠን፤ ስለዚህ ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ እንድትመጡ’ እንደሚለን እንዴት ልናውቅ እንችል ነበር?”