እነርሱም “እያንዳንዳችን ሕልም አየን፤ ነገር ግን የእያንዳንዳችንን ሕልም የሚተረጒም ማንም የለም” አሉት። ዮሴፍም “ሕልም የመተርጐም ችሎታ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ የእያንዳንዳችሁን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።
ዘፍጥረት 41:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም ዮሴፍን “ሕልም አይቼ ነበር፤ ነገር ግን ማንም ሊተረጒመው አልቻለም፤ አንተ ሕልም የመተርጐም ችሎታ እንዳለህ ሰምቼአለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም ዮሴፍን፣ “ሕልም አይቼ ነበር፤ ሕልሜን ሊተረጕምልኝ የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም፤ አንተ ግን ሕልም ሲነገርህ የመተርጐም ችሎታ እንዳለህ ሰማሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ዮሴፍን፥ “ሕልም አይቼ ነበር፤ ሕልሜን ሊተረጉምልኝ የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም፤ አንተ ግን ሕልም ሲነገርህ የመተርጐም ችሎታ እንዳለህ ሰማሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፥ “ሕልምን አየሁ፤ የሚተረጕምልኝም አጣሁ፤ ሕልምን እንደ ሰማህ፥ እንደ ተረጐምህም ስለ አንተ ሰማሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፦ ሕልምን አየሁ የሚተረጕመውም አልተገኘም ሕልምን እንደ ሰማህ እንደ ተረጎምህም ስለ አንተ ሰማሁ። |
እነርሱም “እያንዳንዳችን ሕልም አየን፤ ነገር ግን የእያንዳንዳችንን ሕልም የሚተረጒም ማንም የለም” አሉት። ዮሴፍም “ሕልም የመተርጐም ችሎታ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ የእያንዳንዳችሁን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።
ጠዋት ከመኝታው ሲነሣ መንፈሱ ታወከ፤ ስለዚህ በግብጽ ምድር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች ሁሉ አስጠርቶ ሕልሙን ነገራቸው፤ ነገር ግን የሕልሞቹን ትርጒም ለመግለጥ የቻለ አንድ እንኳ አልነበረም።
መንፈሳዊ አማካሪው ዘካርያስ በሕይወት እስከ ነበረበት ዘመን ድረስ ዖዝያ እግዚአብሔርን በታማኝነት ያገለግል ነበር፤ እግዚአብሔርም ባረከው።
“እንግዲህ እኔ ንጉሥ ናቡከደነፆር ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ አንተም ብልጣሶር ሆይ! ትርጒሙን ንገረኝ፤ በመንግሥቴ ያሉት ጠቢባን ትርጒሙን ሊነግሩኝ አይችሉም፤ አንተ ግን የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ላይ ስላለ ልትነግረኝ ትችላለህ።”
‘የጠቢባን አለቃ የሆንክ ብልጣሶር ሆይ፥ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ላይ ስላለ ምሥጢር ሁሉ ለአንተ ሰውር እንደማይሆን ዐውቃለሁ፤ እነሆ፥ ያየሁትን ሕልም ልንገርህና ተርጒምልኝ።’
እርሱ ሕልምን በመተርጐም፥ እንቆቅልሽን በመፍታትና የተሰወረውን ምሥጢር ገልጦ በማስረዳት ልዩ ችሎታ ያለው ጥበበኛና ብልኅ ሰው ነው፤ ስለዚህ ያንን አባትህ ናቡከደነፆር ‘ብልጣሶር’ ብሎ የሠየመውን ዳንኤልን አስጠራ፤ እርሱ ይህን ሁሉ ነገር ተርጒሞ ያስረዳሃል።”
አንተ ግን የተሰወረውን ነገር የመተርጐምና አስቸጋሪ የሆነውን ነገር ሁሉ የመፍታት ችሎታ እንዳለህ ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ይህን ጽሕፈት አንብበህ ትርጒሙን ብትነግረኝ፥ ሐምራዊ መጐናጸፊያ እንድትለብስ፤ የወርቅ ኒሻን በአንገትህ እንድታደርግና በመንግሥቴም ሥልጣን ሦስተኛውን ማዕርግ እንድትይዝ አደርጋለሁ።”