ዘፍጥረት 40:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይን ጠጅ አሳላፊው ግን ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ስለ ዮሴፍ የሆነውን ሁሉ ረሳ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሆነው ሆኖ፣ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ረሳው እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሆነው ሆኖ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ረሳው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠጅ አሳላፊዎች አለቃ ግን ዮሴፍን አላሰበውም፤ ረሳው እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጠጅ አሳላፊዎች አለቃ ግን ዮሴፍን አላሰበውም ረሳው እንጂ። |
ንጉሡም “ታዲያ፥ ይህን በማድረጉ ለመርዶክዮስ የሰጠነው ዕውቅናና ክብር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ። አገልጋዮቹም “ለእርሱ የተደረገለት ምንም ነገር የለም” ሲሉ መለሱለት።
የወይን ጠጁን በብርሌ ሳይሆን በገምቦ ትጠጣላችሁ፤ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ሽቶ ትቀባላችሁ፤ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ስለ ደረሰው ጥፋት ግን ፈጽሞ አታዝኑም፤ ይህን ሁሉ ስለምታደርጉ ወዮላችሁ!