ዘፍጥረት 40:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍም “የሕልሙ ትርጒም እንዲህ ነው፤ ሦስት መሶቦች ሦስት ቀኖች ናቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “የሕልሙ ፍች ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም መልሶ እንዲህ አለው፥ “የሕልምህ ትርጓሜው ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዚህ ትርጓሜው ይህ ነው ሦስት መሶብ ሦስት ቀን ነው። |
ከሁሉ በላይ ባለው መሶብ ውስጥ ለፈርዖን የተዘጋጀ ልዩ ልዩ ምግብ ነበረበት፤ ነገር ግን ወፎች ምግቡን ከመሶቡ እያነሡ ይበሉት ነበር።’ ”
የዘበኞች አለቃ አገልጋይ የነበረ አንድ ወጣት ዕብራዊ ከእኛ ጋር በእስር ቤት ነበር፤ የእያንዳንዳችንን ሕልም ለእርሱ ነገርነውና ተረጐመልን።
ሁሉም አንድ ዐይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ የጠጡትም ይከተላቸው ከነበረው ከዚያ ከመንፈሳዊ አለት የመነጨ ነበር፤ ያም አለት ራሱ ክርስቶስ ነበር።