እንዲህም አሉ፦ “ኑ አንድ ከተማ እንመሥርት፤ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ እንዳንበታተን ስማችንን እናስጠራ።”
ዘፍጥረት 4:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃየል ሚስቱን ከተገናኘ በኋላ ፀነሰች ሔኖክንም ወለደች፤ ቃየል ከተማን መሠረተ፤ በልጁም ስም “ሔኖክ” ብሎ ጠራት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃየን ሚስቱን ተገናኛት፤ እርሷም ፀንሳ ሔኖክን ወለደች። ቃየን የቈረቈረውን ከተማ በልጁ ስም ሔኖክ ብሎ ጠራው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃየንም ሚስቱን አወቀ፥ ፀነሰችም፥ ሔኖክንም ወለደች፤ ከተማም መሠረተ፤ ከተማይቱንም በልጁም ስም “ሔኖክ” ብሎ ጠራት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃየልም ሚስቱን ዐወቃት፤ ፀነስችም፤ ሄኖሕንም ወለደች። ከተማም ሠራ፤ የከተማይቱንም ስም በልጁ ስም “ሄኖሕ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃየንም ሚስቱን አወቀ ፀነሰችም፤ ሄኖሕንም ወለደች። ከተማም ሠራ፤ የከተማይቱንም ስም በልጅ ስም ሄኖሕ አላት። |
እንዲህም አሉ፦ “ኑ አንድ ከተማ እንመሥርት፤ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ እንዳንበታተን ስማችንን እናስጠራ።”
አቤሴሎም ስሙን የሚያስጠራለት ወንድ ልጅ አልነበረውም፤ ስለዚህም በሕይወት በነበረበት ዘመን “የንጉሥ ሸለቆ” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ለራሱ ሐውልት አሠርቶ ነበር፤ በራሱም ስም ሰይሞት ስለ ነበር እስከ ዛሬ ድረስ “የአቤሴሎም ሐውልት” እየተባለ ይጠራል።
ንጉሡም እንዲህ አለ፦ “ይህችን ታላቋን ባቢሎን የነገሥታት መኖሪያና ዋና ከተማ ሆና የእኔ ክብርና ግርማ እንዲገለጥባት በሥልጣኔ የሠራኋት እኔ አይደለሁምን?”