በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በአንተ ዘርና በእርስዋ ዘር መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ። የእርስዋ ዘር የአንተን ራስ ይቀጠቅጣል፤ አንተም የእርስዋን ዘር ተረከዝ ትነክሳለህ።”
ዘፍጥረት 4:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዳም ከሚስቱ ከሔዋን ጋር ግንኙነት አደረገ፤ እርስዋም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “በእግዚአብሔር ርዳታ ወንድ ልጅ አገኘሁ” ስትል “ቃየል” የሚል ስም አወጣችለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዳም ሚስቱን ሔዋንን ተገናኛት፤ እርሷም ፀንሳ ቃየንን ወለደች፤ “በእግዚአብሔር ርዳታ ወንድ ልጅ አገኘሁ” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፥ እሷም ፀነሰች፥ ቃየንንም ወለደች። እርሷም፦ “ወንድ ልጅ በጌታ ርዳታ አገኘሁ” አለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዳምም ሚስቱን ሔዋንን ዐወቃት፤ ፀነሰችም፤ ቃየልንም ወለደችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ ፀነሰችም፤ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች። |
በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በአንተ ዘርና በእርስዋ ዘር መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ። የእርስዋ ዘር የአንተን ራስ ይቀጠቅጣል፤ አንተም የእርስዋን ዘር ተረከዝ ትነክሳለህ።”
አዳምንም ካስወጣው በኋላ ከዔደን የአትክልት ቦታ በስተ ምሥራቅ በኩል ኪሩቤል የተባሉትን መላእክትንና በየአቅጣጫው እየተገለባበጠ እንደ እሳት የሚንበለበለውን ሰይፍ አኖረ፤ ይህንንም ያደረገው ማንም ወደ ሕይወት ዛፍ እንዳይጠጋ ነው።
አዳምና ሔዋን ሲገናኙ እንደገና ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ እርስዋም “ቃየል በገደለው በአቤል ምትክ እግዚአብሔር ወንድ ልጅ ሰጠኝ” ስትል “ሤት” የሚል ስም አወጣችለት።
የሰይጣን ወገን እንደ ነበረውና ወንድሙን እንደ ገደለው እንደ ቃየል መሆን አይገባንም፤ እርሱ ወንድሙን ስለምን ገደለው? የእርሱ ሥራ ክፉ ስለ ነበረና የወንድሙ ሥራ ግን ትክክል ስለ ነበረ ነው።