ያዕቆብ ልጁ ዲና ክብረ ንጽሕናዋ እንደ ተደፈረ ሰማ፤ ነገር ግን ወንዶች ልጆቹ የከብት መንጋ ይዘው ተሰማርተው ስለ ነበር፥ እነርሱ እስከሚመጡ ዝም ብሎ ቈየ፤
ዘፍጥረት 34:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የሴኬም አባት ሐሞር፥ ያዕቆብን ለማነጋገር ወጣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የሴኬም አባት ኤሞር፣ ያዕቆብን ሊያነጋግረው ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሴኬም አባት ኤሞርም ይነግረው ዘንድ ወደ ያዕቆብ ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሴኬም አባት ኤሞርም ይነግረው ዘንድ ወደ ያዕቆብ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሴኬም አባት ኤሞርም ይነግረው ዘንድ ወደ ያዕቆብ ወጣ። |
ያዕቆብ ልጁ ዲና ክብረ ንጽሕናዋ እንደ ተደፈረ ሰማ፤ ነገር ግን ወንዶች ልጆቹ የከብት መንጋ ይዘው ተሰማርተው ስለ ነበር፥ እነርሱ እስከሚመጡ ዝም ብሎ ቈየ፤
ልክ በዚያኑ ጊዜ የያዕቆብ ልጆች ከተሰማሩበት መጡ፤ ስለ ተፈጸመው ድርጊት በሰሙ ጊዜ እጅግ ደነገጡ፤ ይህ ነገር መደረግ ስላልነበረበት ሴኬም የያዕቆብን ልጅ በመድፈር የእስራኤልን ሕዝብ በማዋረዱም እጅግ ተቈጡ።
የዓቤድ ልጅ ጋዓልም እንዲህ አለ፦ “አቤሜሌክ ማን ነው? እኛ የሴኬም ሰዎች ለእርሱ የምንገዛው ለምንድነው? የጌዴዎን ልጅና የእርሱ የጦር መሪ ዜቡር የሐሞርን አባት ሴኬምን ያገለገሉ አይደሉምን? ለምን ለእርሱ እንታዘዛለን? ይልቅስ የጐሣችሁ መሥራች ለሆነው ለሴኬም አባት ለሐሞር ታማኞች ሁኑ።