ዘፍጥረት 33:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ልያና ልጆችዋ ቀርበው እጅ ነሡ፤ በመጨረሻም ዮሴፍና ራሔል ቀርበው እጅ ነሡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ልያና ልጆቿ መጥተው እጅ ነሡ፤ በመጨረሻም ዮሴፍና ራሔል መጡ፤ እነርሱም ቀርበው እጅ ነሡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ልያና ልጆችዋ ቀረበው እጅ ነሡ፥ በመጨረሻም ዮሴፍና ራሔል ቀርበው እጅ ነሡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ልያና ልጆችዋ ቀርበው ሰገዱለት፤ ከዚያም በኋላ ዮሴፍና ራሔል ቀርበው ሰገዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ልያና ልጆችዋ ቀረበው ሰገዱ ከዚይም በኍላ ዮሴፍና ራሔል ቀርበው ሰገዱ። |
ዔሳውም “እፊት እፊትስ እየተነዳ ሲሄድ ያየሁት የእንስሶች መንጋ ምንድን ነው?” አለ። ያዕቆብም “ጌታዬ ሆይ፥ እርሱ በአንተ ፊት ሞገስ እንዳገኝ የላክሁልህ ነው” አለ።