ዘፍጥረት 31:54 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተራራውም ላይ ያዕቆብ መሥዋዕት አቀረበ፤ ሰዎቹን ሁሉ ጠርቶም ምግብ እንዲመገቡ አደረገ፤ ከበሉም በኋላ ሌሊቱን በዚያ አሳለፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ በኰረብታማው አገር ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጋበዛቸው፤ እነርሱም ከበሉ በኋላ እዚያው ዐደሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም በተራራው ላይ መሥዋዕትን አቀረበ፥ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጠራ፥ እነርሱም ምግብ ተመገቡ፥ በዚያም በተራራ ሌሊቱን ሙሉ አሳለፉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም በተራራው ላይ መሥዋዕትን ሠዋ፤ ወንድሞቹንም ጠራ፤ እነርሱም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚያም በተራራው አደሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም በተራራው ላይ መሥዋዕትን ሠዋ ወንድሞቹንም እንጀራ እንዲበሉ ጠራ እነርሱም እንጀራን በሉ በዚያም በተራራ አደሩ። |
ከዚህ በኋላ ምሳ ለመብላት ተቀመጡ፤ በሚመገቡበትም ጊዜ እስማኤላውያን ነጋዴዎችን በሩቅ አዩ፤ እነርሱም በግመሎቻቸው ቅመማ ቅመም፥ በለሳን፥ ከርቤም ጭነው ከገለዓድ ወደ ግብጽ የሚጓዙ ነበሩ።
ከዚህም በኋላ የትሮ የሙሴ ዐማት በሙሉ የሚቃጠል ቊርባንና ሌላም ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አመጣ፤ አሮንና የእስራኤል አለቆችም ሁሉ የተቀደሰውን ምግብ በአምልኮት ሥርዓት በእግዚአብሔር ፊት ለመመገብ ከሙሴ ዐማት ጋር መጡ።
የሆነ ሆኖ የሕዝቡ መሪ የተቀደሰውን የመሥዋዕት ኅብስት ለመብላት በዚያ መቀመጥ ይችላል፤ በመግቢያውም ክፍል ውስጠኛ ጫፍ በሚገኘው መተላለፊያ በኩል መግባትና መውጣት ይፈቀድለታል።”