ዘፍጥረት 30:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተን በማገልገል ያገኘኋቸውን ሚስቶቼንና ልጆቼን ስጠኝና ልሂድ፤ ምን ያኽል አገልግሎት እንዳበረከትኩልህ ታውቃለህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የድካሜ ዋጋ የሆኑትን ሚስቶቼንና ልጆቼን ስጠኝና ይዣቸው ልሂድ፤ መቼም የቱን ያህል እንዳገለገልሁህ ታውቃለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ እነርሱ የተገዛሁላቸውን ሚስቶችንና ልጆቼን ስጠኝና ልሂድ፥ የተገዛሁልህን መገዛት ታውቃለህና።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ እነርሱ የተገዛሁላቸውን ሚስቶቼንና ልጆችን ስጠኝና ልሂድ፤ የተገዛሁልህን መገዛት ታውቃለህና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ እነርሱ የተገዛሁላቸውን ሚስቶችንና ልጆቼን ስጠኝና ልሂድ፤ የተገዛሁልህን መገዛት ታውቃለህና። |
ከዚህ በኋላ ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “ስለምን እንዲህ አድርገህ አታለልከኝ? ሴቶች ልጆቼንስ በጦርነት እንደ ተማረኩ ያኽል ይዘሃቸው ለምን ሄድክ?